መካከለኛ ምስራቅ

አሜሪካ የኢራን ድሮን መትታ መጣሏ ገለፀች።

የኢራን መንግስት በዙሪያው ያለው ነገር የለም።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 27/05/2018፡- አሜሪካ ወደ ጦር መርከቧ ሲበር የነበረን የኢራን ድሮን መትታ መጣሏን አስታወቀች።

አሜሪካ፤ በአረቢያ ባህር ላይ ወደሚገኘው አውሮፕላን ተሸካሚ መርከቧ “በኃይል ሲቃረብ” የነበረ የኢራን ድሮንን መትታ መጣሏን የአገሪቱ ጦር ቃል አቀባይ ገለጹ።

ድሮኑ ላይ ጥቃት የፈጸመው ‘ዩኤስኤስ አብርሀም’ ሊንከን ከተባለው ግዙፉ የአሜሪካ የጦር መርከብ የተነሳ ኤፍ-35 ሲ የተሰኘ የራዳር እይታን የሚያመልጥ ተዋጊ ጄት እንደሆነ የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ቃል አቀባይ ካፒቴን ቲም ሀውኪንስ ተናግረዋል።

እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ የማክሰኞ ዕለቱ “ራስን የመከላከል እርምጃ” የተወሰደው አውሮፕላን ተሸካሚውን መርከብ እና ሠራተኞቹን ለመጠበቅ ሲባል ነው።

ሲበር የነበረበት “ዓላማ ግልጽ እንዳልሆነ” የተገለጸው ድሮን በሚጠጋበት ወቅት የአሜሪካ የጦር መርከብ ከኢራን የባህር ዳርቻ በግምት 805 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደነበረም ተገልጿል።

ከዚህ ክስተት ጋር በተያያዘ የተጎዳ የአሜሪካ ወታደርም ሆነ ንብረት የለም ተብሏል።

ይህ ሁኔታ የተፈጠረው በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ያለው ውጥረት እየበረታ መሆኑን ተከትሎ ዋሽንግተን በቀጣናው ያላትን ወታደራዊ ኃይል እያጠናከረች ባለችበት ወቅት ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates