አፍሪካ
የሱዳን ጦር የደቡብ ኮርዶፋን ዋና ከተማ የሆነችው ካዱግሊ ከፈጣን ድጋፍ ሐይሉ ነፃ ማውጣቱ ገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 26/05/2018፡- ለሶስት ቀናት ከፈጀ ከባድ ውጊያ በኋላ፣ በተባበሩት አሃዶች የተደገፈው የሱዳን ጦር የደቡብ ኮርዶፋን ዋና ከተማ የሆነችው ከተማ በመቆጣጠር የዳላንግ-ካዱግሊ መንገድን እንደገና ክፍት እንዲሆን ማድረጉን አስታውቋል።
ዛሬ ጠዋት ኃይሎች ወደ ዴይሾል በማቅናት በአል-ኮ አል-ሃሚ እና በአል-ሊሳን ዳቂቅ ላይ ከፍተኛ ውጊያ በማድረግ ወደ ከተማዋ መግባታቸው ታውቋል።
በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚደገፈው የRSF ሚሊሻ ለመሸሽ ሲሞክር፣ ከአል-ኦቤይድ የተንቀሳቃሽ ኃይል አድፍጦ አብዛኛዎቹን ሰራዊታቸውን አጥፍቶ በርካታ ተዋጊዎችን መያዙ ተዘግቧል።
ይህ ድል የሱዳን ሰራዊት በአሁን ጊዜ በፈጣን ድጋፍ ሐይሉ የበላይነት እየተጎናፀፈ መሆኑን ማሳያ ተደርጎ እየተወሰደ ነው።



