ዲፕሎማሲ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከዩናይትድ ኪንግደም የኮመንዌልዝ፣ ልማት ጉዳዮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መወያየታቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/05/2018፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከዩናይትድ ኪንግደም የኮመንዌልዝ፣ ልማት ጉዳዮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መወያየታቸው ተገለፀ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የዩናይትድ ኪንግደም የኮመንዌልዝ፣ ልማት ጉዳዮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቬት ኩፐርን አግኝቼ በቁልፍ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል።

‎ከውይይቱ ጎን ለጎን በተካሄደው የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ማዕቀፍ ሥር የኢንቨስትመንት እና ኃብት አስተዳደር የቴክኒካል ትብብር የመግባቢያ ሥምምነት እና የሁለት የጋራ የልማት ስምምነቶች ፊርማ መርሃ ግብር ላይ መገኘታቸውንም ገልጸዋል።

ስምምነቶቹ የሁርሶ-አይሻ 400 ኪሎ ቮልት እና የደገሃቡር-ቀብሪደሃር 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

እነዚህ ስምምነቶች ትብብርን በማጠናከር እና ስትራቴጂያዊ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ ርምጃን የሚያሳዩ ናቸው ሲሉ የመንግስት ሚድያዎች ዘግቧል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates