ኢትዮጵያ
ላለፉት አራት ቀናት ወደ ትግራይ ተቋርጦ የነበረው የአየር በረራ ነገ ጥር 26 እንደምጀምር ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/05/2018፡- ላለፉት አራት ቀናት ወደ ትግራይ ተቋርጦ የነበረው የአየር በረራ ነገ ጥር 26 እንደምጀምር ተገለፀ።
“ባልታቀደ ሁኔታ” በሚል ጥር 21 ቀን 2018 ዓ/ም ወደ ትግራይ ስያደርገው የነበረው በረራ ያቋረጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነገ ጥር 26 ዳግም በረራ እንደሚጀምር የወጡ መረጃዎች አሳይቷል።
አየር መንገዱ በረራው ሲያቋርጥ ይሁን አሁኖም ሲጀምር በይፋ መግለጫ ባያወጣም በመቐለ ከተማ የሚገኘው የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሰራተኞች ነገ ማክሰኞ ስራ እንዲገቡ እንደተነገራቸው ታውቋል።
ሰራተኞቹ ባለፈው ሳምንት ስራ እንደሌለ እና ወደ ቢሮ እንዳይገቡ አዲስ አበባ ከሚገኘው መሥሪያ ቤት ከመነገራቸው ውጪ ምክንያቱ እንደማያውቁ መግለፃቸው ይታወሳል።
ሆኖም በረራው የተቋረጠው በትግራይ አንዳንድ አከባቢዎች በተለይ በፀለምት እና ደቡባዊ ዞን በመከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሐይሎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
ከአየር በረራ በተጨማሪ በትግራይ የባንኮች አገልግሎትም በጥሬ ገንዘብ እጥረት ተቋርጦ እንደሚገኝ ይታወቃል።
የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ በፀለምት የተከሰተውን ግጭት እንዲቆምና በሰላማዊ መንገድ ነገሮች እንዲፈቱ ፀለምት የገባውን የትግራይ ሐይል እንዲወጣ መደረጉ መግለፃቸው ይታወሳል።



