ፖለቲካ

የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መንግሥት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚበትን ድንጋጌ ማውጣቱ ታወቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 22/05/2018፡- በካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ የሚመራው የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መንግሥት በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ስብስቦች የሚበትን ድንጋጌ አፀድቀዋል፡፡

የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች መበራከት ለክፍፍል እና ለማህበራዊ ትስስር መላላት ምክንያት ሆኗል ብለዋል። በወታደራዊ ኃይል የሚመራው የቡርኪና ፋሶ መንግሥት፣ ከአራት ዓመታት በፊት በተደረገ መፈንቅለ መንግስት ምክንያት እንቅስቃሴያቸውን ታግዶ የቆዩ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች በይፋ የሚያፈርስ ድንጋጌ ማውጣቱ ተሰምቷል።

የቡርኪናፋሶ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ድንጋጌውን ያጸደቀው ትናንት ሐሙስ ሲሆን፤ ይህም የሆነው መንግሥት ከአልቃይዳ እና ከአይኤስ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ አማጺያንን ለመቆጣጠር በሚታገልበት እና የተቃውሞ ድምጾችን በማፈን ላይ ነው በሚባልበት በዚህ ወቅት መሆኑ ትኩረት ሳቢ አድርጎታል።

አዲሱ ድንጋጌ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ስብስቦች ይበትናል፤ የፓርቲዎቹ ንብረቶች በሙሉ ወደ መንግሥት ይዞታነት እንዲዛወሩም ወይም እንዲወረሱ ያዛል።

ከአራት ዓመታት በፊት በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ስር ከመውደቋ አሰደቀድሞ ከ100 በላይ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች የነበሯት ቡርኪናፋሶ፤ እ.አ.አ. በ2020 በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ 15 ፓርቲዎች ብቻ በፓርላማ ውስጥ መቀመጫ ማግኘት ችለውም ነበር።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates