አፍሪካ

ኢጋድ የሱዳኑ ፈጣን ድጋፍ ሐይል የፈፀማቸው ወንጀሎችን ለመጀመሪያ ጊዜ አወገዘ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 22/05/2018፡- የመስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ሐሙስ ዕለት ባወጣው መግለጫ የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች የፈጸሙትን ወንጀሎች በይፋ ማውገዙን አስታውቋል፤ ይህ እርምጃ በሱዳን መንግስት ወዲያውኑ ተቀባይነት አግኝቷል።

ኢጋድ የሱዳንን ጦር ሳይጠቅስ ፈጣን ድጋፍ ሐይሉን ብቻ ተጠያቂ የሚያደርግ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፣ ሁለቱም ተዋጊ ወገኖች ጦርነቱን እንዲያቆሙ እና የፖለቲካ ውሳኔን እንዲከተሉ ጥሪ አቅርቧል።

የኢጋድ መግለጫ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ኢድሪስ የአሁኑ የኢጋድ ሊቀመንበር ወደ ሆነችው ጅቡቲ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ ነው ተብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ኢድሪስ በጅቡቲ ቆይታቸው ከኢጋድ ዋና ፀሐፊው ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና ከፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

“የኢጋድ ሴክሬታሪያት በፈጣን የድጋፍ ኃይሎች የሚፈጸሙትን ሁሉንም አይነት ጥሰቶች ያወግዛል እንዲሁም ለሱዳን ሪፐብሊክ አንድነት እና ሉዓላዊነት ሙሉ ድጋፍ እንዳለው ያረጋግጣል” ሲል ኢጋድ በይፋዊ መግለጫው አስታውቋል።

ድርጅቱ የሱዳንን ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት የወሰደውን ብሔራዊ ተነሳሽነት ተቀብሎ ኢጋድ የሱዳን ሪፐብሊክ ወደ ተቋማዊ ማዕቀፉ ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኢድሪስ ሱዳን ወደ አፍሪካ ሕብረትና ኢጋድ እንድትመለስ ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

የኢጋድ መግለጫን ተከትሎ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፍጥነት መግለጫ ያወጣ ሲሆን ለፕሬዚዳንት ጌሌህ እና ለኢጋድ ዋና ፀሐፊ ላሳዩት አቋም ምስጋናውን አቅርቧል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates