ግዙፉ አውሮፕላን ተሸካሚ የአሜሪካ የጦር መርከብ መካከለኛው ምሥራቅ መድረሱ ታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/05/2018፡- የባሕር ላይ ተዋጊ መርከቦችን ያስከተለው ግዙፉ የአሜሪካን ተዋጊ አውሮፕላኖች ጫኝ የጦር መርከብ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ መድረሱን ሁለት የአሜሪካ ባለሥልጣናት ለሮይተርስ የዜና ወኪል አስታወቁ።
ለሳምንታት በኢራን የተካሄደውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በኢራን ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ሲናገሩ የነበሩት ፕሬዝዳንት ትራምፕ መርከቦቹ ወደ አካባቢው መላካቸውን ባለፈው ሳምንት አሳውቀው ነበረ።
ይህ ክስተት በመካከለኛው ምስራቅ ሌላ ደም አፋሳሽ ግጭት እንዳይከሰት የተሰጋ ሲሆን ኢራን ራሷን ለመከላከል እንደምትገደድ አስጠንቅቃለች።
ይህ ሌሎች አካላትም ሊሳተፉበት እንደሚችል እየተነገረለት ያለው ውዝግብ አሜሪካ ኢራንን ካጠቃች ሔዝቦላህ እና ሌሎች ቡድኖች ከኢራን ጎን እንደሚቆሙ እየገለፁ ነው።
አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ከፈጸመች ኢራንን እንደሚደግፉ ሔዝቦላህ እና በኢራቅ የሚገኙ ታጣቂ ቡድኖች አስታውቋል።
የሊባኖሱ ሔዝቦላህን ጨምሮ በመካከለኛው ምሥራቅ ያሉ በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች ጥቃት ከተፈጸመባት ከኢራን ጎን እንደሚቆሙ እየገለጹ ነው።
የሔዝቦላህ ዋና ፀሐፊ ናይም ቃሲም በኢራን ላይ የሚፈጸም ጥቃት በእነሱም ላይ እንደተፈጸመ የእንደሚቆጥሩት ገልጸው፤ የአዲስ ጦርነት ነበልባል አጠቃላይ ቀጣናውን የሚለበልብ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በኢራን የሚደገፉ ኢራቅ ውስጥ የሚገኙ ታጣቂ ቡድኖች በተመሳሳይ በኢራን ላይ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጥቃት የሚፈጸም ከሆነ ከኢራን ጎን ለመሰለፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።



