መካከለኛ ምስራቅ

ኢራን ለእስራኤል ‘ሲሰልል’ ነበር የተባለ ግለሰብን በሞት ቀጣች።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/05/2018፡- ለእስራኤል የስለላ ተቋም ሞሳድ ኢራን ውስጥ ሲሰልል ከወራት በፊት ተይዟል ተብሎ በቁጥጥር ሥር የነበረ አንድ ግለሰብ በሞት መቀጣቱን የኢራን መንግሥት አስታወቀ።

‘ሚዛን’ የተባለው የኢራን የፍትሕ ተቋማት የዜና ምንጭ እንደዘገበው ሃሚድሬዛ ሳቤት ኢስማኤልፑር የተባለው ግለሰብ ባለፈው ዓመት ግንቦት ላይ ነበር በስለላ ተከስሶ የተያዘው።

የኢራን ፍትሕ ተቋም እንዳለው ግለሰቡ እስራኤል በአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር የሚሳዔል ማዕከላት ላይ አሻጥር እንድትፈጽም ምሥጢራዊ ሰነዶችን እና መረጃዎችን ማስተላለፍ ውስጥ ተሳትፏል የሚል ክስ ቀርቦበታል።

በወጣው ዜና ላይ እንደተጠቀሰው የኢራን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በግለሰቡ ላይ ያሳለፈው የቅጣት ውሳኔ ከተገመገመ በኋላ ግለሰቡ በስቅላት ተቀጥቷል።

አሁን የሞት ቅጣቱ የተፈጸመበት ሃሚድ ሬዛ ሳቤት ኢስማኤልፑር ለእስራኤል በመሰለል በሚል ክስ በዚህ ወር በሞት የተቀጣ ሁለተኛው ሰው ነው።

ባለፈው ዓመት ሰኔ ላይ እስራኤል እና ኢራን ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ለእስራኤል ሲሰልሉ ነበር በሚል ተከስሰው በሞት የተቀጡ ኢራናውያን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates