የሱዳን ሰራዊት ከፍተኛ ድል እየተቀዳጀ መሆኑን አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 19/05/2018፡- የሱዳን ጦር ባወጣው መግለጫ፣ ለሁለት ዓመት ተኩል ከበባ ውስጥ የነበረችውን በደቡብ ኮርዶፋን ግዛት የምትገኘው ዲሊንግ ከተማ ባደረገው ኦፕሬሽን ከፈጣን ድጋፍ ሐይሉ ነፃ ማውጣቱ አስታውቋል።
ጦሩ ባካሄደው ስኬታማ ወታደራዊ ኦፕሬሽን “በጠላት ኃይሎች ላይ ከባድ ኪሳራ በማድረስ” የዲሊንግ መንገድን መክፈት መቻሉን ገልጿል።
ይህ ድል ከተረጋገጠ በኃላ፣ ጦሩ ወደ ዲሊንግ የሚያስገቡትን የሰሜን እና የደቡብ አቅጣጫዎች ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ያስችለዋል ተብሏል።
ዲሊንግ፣ በከበባ ውስጥ በምትገኘው የግዛቱ ዋና ከተማ ካዱግሊ እና በሰሜን ኮርዶፋን ዋና ከተማ ኤል-ኦቤይድ መካከል የምትገኝ ስትራቴጂካዊ ከተማ መሆኗ የተገለፀ ሲሆን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እነዚህን አካባቢዎች ከቦ ቆይቷል።
በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቁ ቪዲዮዎች፣ የጦሩ አባላት በዲሊንግ ከተማ በመኪና ላይ ሆነው ደስታቸው ሲያከብሩ እና ነዋሪዎች በደስታ ሲቀበሏቸው ያሳያሉ።
ይህ የጦሩ እርምጃ የተከተለው፣ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በሰፊው የኮርዶፋን ግዛት እያደረገ የነበረውን ፈጣን ግስጋሴ ለመግታት የሚደረገውን ጥረት አካል እንደሆነ ተገልጿል።
በጄነራል ዳጋሎ የሚመራው ሐይል ባለፈው ጥቅምት በምዕራብ ዳርፉር የሚገኘውን የመጨረሻውን የጦር ሰፈር ከተቆጣጠረ በኋላ፣ ትኩረቱን ወደ ምስራቅ በማዞር በምዕራብ ኮርዶፋን እና የሱዳን ትልቁ የነዳጅ ማውጫ በሆነችው በሄግሊግ ላይ ቁጥጥሩን አጠናክሮ ነበር።



