ኤስያ

በቻይና ከፍተኛ ወታደራዊ ቀውስ መከሰቱ ተሰማ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 18/05/2018፡- ቻይና የሀገሪቱ ከፍተኛ ጄነራል ላይ ምርመራ መጀመሯ ተገልጿል።

ቻይና የሀገሪቱ ከፍተኛው ወታደራዊ ማዕረግ ባለቤት የሆኑት ጄነራል “የዲሲፕሊን እና የሕግ ጥሰት ፈጽመዋል” በሚል ምርመራ እንደከፈትባቸው አስታወቀች።

የተከሰሱት ጄነራል ዣንግ ዩዢያ የፕሬዝደንት ዢ ጂንፒንግ የቅርብ ሰው ሲሆኑ፣ የተከሰሱበት ዝርዝር መረጃ አልተገለፀም።

ሌላኛው ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን ጄነራል ሊዩ ዤንሊም ምርመራ እንደተከፈተባቸው የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምንም እንኳ ሚኒስቴሩ ዝርዝር መረጃ ባይሰጥም ብዙውን ጊዜ ባለሥልጣናል የዲሲፕሊን ጥሰት ፈጽመዋል ተብለው የሚከሰሱት በሙስና ሲጠረጠሩ ነው።

ቻይና ካለፈው ጥቅምት ጀምሮ ዘጠኝ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችን ከሥልጣን ያነሳች ሲሆን፣ ይህ ለዓመታት ታይቶ የማይታወቅ ነው ተብሏል።

የ75 ዓመቱ ዣንግ የማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር ሲሆኑ የሀገሪቱ ውሳኔ ሰጪ አካል የሆነው ፖሊት ቢሮ አባልም መሆናቸው መረጃዎች አሳይቷል።

Show More

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates