አፍሪካ
በደቡብ ሱዳን ዳግም የተከሰተው ግጭት ከ180,000 በላይ ሰዎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 18/05/2018፡- የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከዋና ከተማዋ ጁባ በስተሰሜን በሚገኘው የጆንግሌይ ግዛት የተከሰተው ግጭት “ከባድ ስጋት” መፍጠሩን ገልጿል።
አጃንስ ፍራንስ ፕረስ እንደዘገበው በሺህ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ቀያቸውን ለቀው ደህንነቱ ወዳልተጠበቀ ቦታ እየሸሹ ነው።
የአይን እማኞች ለዜና ምንጩ እንደተናገሩት ባለፈው ሳምንት የተቃዋሚ ኃይሎች በመንግሥት ወታደሮች ከተባረሩ በኋላ ወጣቱ በሚኖርባት ዱክ አውራጃ ከባድ ውጊያ ተካሂዷል።
“ብዙ ሰዎች ተገድለዋል” ቁጥራቸውም 300 እንደሚጠጋ ተናግሯል።
ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ባለፈው መጋቢት የረጅም ጊዜ ተቀናቃኛቸው ሪክ ማቻርን በቁጥጥር ስር ካዋሉ እና ማቻር በተለያዩ ወንጀሎች ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ በሁለቱ ዋና ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የነበረው የስልጣን መጋራት ስምምነት ሙሉ በሙሉ ፈርሷል።
በሁለቱ ፖለቲከኞች መካከል በተደረገው የአምስት ዓመት የእርስ በርስ ጦርነት 400,000 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር 2018 ዓ/ም በተደረገ የሰላም ስምምነት ነበር ግጭቱ የተቋጨው።



