አፍሪካ

የሱዳን ጦር አዲሱ የአሜሪካ እና የሳውዲ የተኩስ አቁም ምክረ ሀሳብ እያጤነ እንደሆነ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 14/05/2018፡- የሱዳን ጦር በአሜሪካ እና ከሳውዲ አረቢያየቀረበው የተኩስ አቁም ምክረ ሀሳብ ተቀብሎ እያጤነ መሆኑን የመንግስት ምንጭ ጠቅሶየፈረንሳዩ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ ዘግቧል።

የደህንነት እና የመከላከያ ምክር ቤት ከጦር ኃይሉ እና ከአጋር መንግስት ባለስልጣናትን ያካተተ ከፍተኛ ደረጃ የተባለለት ውይይት ለመጀመሪያ ጊዜ በካርቱም የተቀመጠ ሲሆን “ዛሬ የአሜሪካ-ሳውዲ የሰብአዊ ስምምነት እና የተኩስ አቁም ሀሳብን ለመወያየት ስብሰባ እያካሄደ ነው” ሲሉ ማንነታቸውን እንዳይገለፅ የፈለጉት ባለ ስልጣን መናገራቸው መረጃው አመልክቷል።

ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ በሱዳን ጦር እና በፈጣን ድጋፍ ኃይሎች መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞት ዳርጓል፤ ወደ 11 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች አፈናቅሏል።

የጦር ኃይሉ አዛዥ ጄነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ከዚህ ቀፊት የቀረቡት የተኩስ አቁም ምክረ ሐሳቦች ለተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያደላ በማለት ውድቅ በማድረጋቸው ኳድ ተብሎ በሚጠራው የአራት አገሮች ጥምረት የሚመራው ውይይት ለወራት ተቋርጦ ቆይቷል።

አሁን ግን በድጋሚ የሰላም ምክረ ሐሳቡ እየተመለከተው እንደሆነ ተገልጿል።

የሱዳን ሰራዊት በፈጣን ድጋፍ ሐይሉ ድሎች እየተቀናጀሁ እገኛለሁ በሚልበት በዚህ ወቅት የሰላም ስምምነቱ ለመቀበል ወይስ በጄነራል መሐመዳ ሐምዳን ዳጋሎ ጫና ለመፍጠር የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates