ፖለቲካ

በትግራይ ፀጥታ ሐይሎች ተይዘው ላለፉት አራት ቀናት ሳይታዩ የቆዩተ ጄኔራል ጉዑሽ ገብረ ከቤተሰባቸው ጋር ተገናኙ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 13/05/2018፡- ጥር 9 ቀን 2018 ዓ/ም የታሰሩት ጄኔራል ጉዑሽ ገብረ ጥር 10 ቀን በወታደራዊ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆኑ ለጥር 18 ቀጠሮ እንደተሰጣቸው የትግራይ የሰላም እና ደህንነት ቢሮ ገልጿል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሊያገኙዋቸው እንዳልቻሉት ሲገልፁ የቆዩት ቤተሰቦቻቸው ትናንት ጥር 12 ቀን 2018 ዓ/ም እንዳገኙዋቸው እንደተፈቀደላቸው ታውቀዋል፡፡

የጄኔራል ጉዑሽ ገብረ ታናሽ ወንድም አቶ ይብራህ ገብረ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ትናንት ወደ ማምሻው ለአጭር ደቂቃዎች ሊያገኙዋቸው እንደተፈቀደላቸው በመግለፅ ያገኙዋቸው ግን የታሰሩበት ቦታ ሳይሆን በሰሜን ምስራቅ ግንባር ጽ/ቤት እንደነበረ አስታውቀዋል።

ጄኔራል ጉዑሽ በዳህና ሁኔታ እንደሚገኙ የገለፁት ወንድማቸው አቶ ይብራህ ሆኖም በምን ጉዳይ እንደተያዙ እስካሁን እንዳልተገለፀላቸው እንደነገሩዋቸው አብራርተዋል፡፡

ይሁን እንጂ የሰላምና ደህንነት ቢሮው ጄኔራል ጉዑሽ ገብረ ሠራዊቱን በማፍረስ፣ ከጠላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር እና ለአዛዦች ባለመታዘዝ በሦስት ክሶች ተከሰዋል ብሏል።

ጄኔራል ጉዑሽ ገብረ ከተያዙ በኋላ ወደ ኤርትራ ተላልፈው መሰጠታቸውን በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ሲገልፅ የነበረ ቢሆንም ወንድማቸው ግን እኛ ይህንን ወሬ የጭንቀታችን አካል አልነበረም ብለዋል።

ጄኔራል ጉዑሽ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ/ም ኮርና ከዚያ በላይ የሰራዊቱ አመራር የወሰነው ውሳኔ ከተቃወሙት የትግራይ ጦር ከፍተኛ አመራሮች አንዱ ሲሆኑ ከክፍለ ጦር አዛዥነታቸው ተነስቶ ከቆዩ በኃላ ባለፈው ዓመት አጋማሽ በራሳቸወ ወደ አሃዱዋቸው መመለሳቸውን ለሚድያዎች መናገራቸው ተከትሎ በሰራዊቱ ላይ ከፍተኛ ልዩነት ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የትግራይ ፐብሊክ ዲፕለፐማሲ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ጄነራል ጉዑሽ ገብረ፣ ጄነራል ከበደ ፍቃዱ እና ኮሎኔል ገ/ዮሐንስ አባተ (ወዲ አባተ) ከጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንቱ ጄኔራል ታደሰ ወረዳ በማገናኘት እንደታረቁ ገልፆ እንደነበር ይታወሳል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates