ዲፕሎማሲ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) በአዘርባጃን ይፋዊ ጉብኝት እንድያደርጉ ጥሪ ቀረበላቸው።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 12/05/2018፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት የቀረበላቸውን ጥሪ መቀበላቸውን የአዘርባጃን ፕሬስ ኤጀንሲ ዘገበ።
ይህ የጉብኝት ጥሪ የተላለፈው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአዘርባጃኑ ሄይደር አሊዬቭ ፋውንዴሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ከሆኑት ሌይላ አሊዬቫ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።
በውይይታቸውም ወቅት ሌይላ አሊዬቫ የፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭን ሰላምታ ካደረሱ በኋላ ይፋዊ የጉብኝት ጥሪ ማቅረባቸው ታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩም ጥሪውን በመቀበል፤ ለፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ያላቸውን “ከፍተኛ ክብር” መግለጻቸውን ዘገባው አመልክቷል።
ውይይቱ በኢትዮጵያና በአዘርባጃን መካከል ባለው ወቅታዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ትብብሩን ይበልጥ ማስፋፋት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል።



