
ኢትዮ ሞኒተር፡ 12/05/2018፡- ሶማሊያ ከየተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የነበራት ወታደራዊ ስምምነት ካቋረጠች ከሳምንታት በኃላ ነው ከኳታር ጋር ስምምነት መፈፀሟ የተገለፀው።
ይህ ስምምነት በሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትሩ አህመድ ሞአሊም ፊቂ እና በኳታር የመከላከያ ሚኒስትር ሼክ ሳዑድ ቢን አብዱራህማን አል ታኒ የተፈረመው ሲሆን ወታደራዊ ስልጠና እና የልምድ ልውውጥ፣ የመከላከያ አቅምን ማሻሻል፣ የቀጠና ደህንነት ላይ እንደሚያተኩር ተገልጿል።
በቅርቡ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የደህንነት ስምምነቶችን መሰረዝን ተከትሎ፣ ኳታር አሁን በኢሚሬትስ ይሰጥ የነበረው የገንዘብ እና የሥልጠና ክፍተትን ልትሞላ ትችላለች ተብሏል።
ይህ እርምጃ፣ ከሳውዲ አረቢያ ጋር ካለው ግንኙነት ጎን ለጎን፣ በሶማሊያ የመከላከያ ፖሊሲ ውስጥ ትልቅ የቀጠናው ዳግም መደራጀትን ያሳያል የሚል ግምት ተሰጥቷል።
በዶሃ በተፈረመበት ወቅት የሁለቱም ሀገራት ባለስልጣናት ስምምነቱ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።



