መካከለኛ ምስራቅ

በሳውዲ የሚደገፈው የየመን መንግስት የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ሚስጥራዊ እስር ቤቶችን በማስኬድ ላይ ከሰሰ።

 አቡ ዳቢ ክሱን አስተባብላለች።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 12/05/2018፡- በሳውዲ የሚደገፈው የየመን መንግስት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በደቡብ የየመን የወደብ ከተማ ሙካላ አቅራቢያ በሚገኝ የአየር ማረፊያ ሚስጥራዊ እስር ቤት በማስተዳደር ላይ እንደነበረች ከሰሰ።

ይህም በሁለቱ የባህረ ሰላጤ የነዳጅ ሀገራት፣ በሳዑዲ አረቢያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል በተፈጠረው ጥልቅ አለመግባባት ውስጥ ውጥረትን አስነስቷል።

ክሱ የቀረበው በሳውዲ አረቢያ የምስራቅ የየመን ግዛት የሃድራማውት ገዥ ሳሌም አል-ካንባሺ፣ በሳዑዲ መንግስት ባዘጋጀው የሚዲያ ጉዞ ወቅት የሮይተርስ ቡድንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞችን ከሪያድ ወደ የመን ከተማ ሙካላ አቅራቢያ ወደሚገኘው የሪያን አየር ማረፊያ በመላክ ነው።

አል-ካንባሺ በቴሌቪዥን በተላለፈው የፕሬስ ኮንፈረንስ ላይ እንደተናገሩት፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና በዋናው የገንጣይ ቡድን መሪ ላይ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል።

“የተበደሉት ፍትህ እንድያገኙ የጥሰቶችን ፈጻሚዎች፣ አይዳሩስ አል-ዙባይዲ ወይም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ – አባላቱ፣ ባለስልጣናቱ ወይም ለእነሱ የሚሰሩ ሰዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ አስፈላጊ እርምጃዎች ይወሰዳሉ” ብሏል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ግን ክሱን ውድቅ አድርገዋለች።

ኢሚሬትስ ዛሬ ባዘጣችው መግለጫ ክሱ “ሆን ተብሎ የተፈበረኩ ውሸቶችና የተሳሳቱ መረጃዎች ከመሆን ያለፈ ነገር የለም” ብላ ጠርታዋለች።

“የተጠቀሱት ተቋማት ወታደራዊ ማረፊያዎች፣ የኦፕሬሽን ክፍሎች እና የተመሸጉ መጠለያዎች ብቻ ናቸው፣ አንዳንዶቹ ከመሬት በታች የሚገኙ ናቸው – በዓለም ዙሪያ የአየር ማረፊያዎች እና ወታደራዊ ተቋማት የተለመዱ እና ታዋቂ ባህሪያት ናቸው – እናም ከተለመደው ወታደራዊ ሁኔታ በላይ ምንም አይነት አንድምታ የላቸውም” ሲል የኤምሬትስ ሚኒስቴር አስታውቋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates