ዲፕሎማሲ

የሩሲያውን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን “የሰላም ቦርድ” በተሰኘውና ዓለም አቀፍ ግጭቶችን እንዲሳተፉ መጋበዛቸው ትራምፕ አስታወቁ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 12/05/2018፡- ፑቲን “የሰላም ቦርድ” የተሰኘው አዲስ የሰላም ተነሳሽነት ውስጥ እንዲሳተፉ መጋበዛቸውን ትራምፕ ትናንት ሰኞ አረጋገጠዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ ይህ ቦርድ የጋዛን የሰላም ዕቅድ ሁለተኛ ምዕራፍ ጨምሮ የተወሳሰቡ ዓለም አቀፍ ግጭቶችን ለመፍታት ያለመ ነው።

የክሬምሊን ቤተ መንግስት ፕሬዝዳንት ፑቲን ጥሪው እንደደረሳቸው እና ሞስኮ ሃሳቡን እየገመገመች መሆኗን አስታውቋል።

ክሬምሊን አክሎም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ከዋሽንግተን ጋር የወደፊት ግንኙነቶች እንደሚኖሩ ተስፋ እንዳለው ገልጿል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ አያይዘውም የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንም የዚህ “የሰላም ቦርድ” አባል እንደሚሆኑ ጠቁመዋል።

ፕሬዝዳንት ማክሮን ጥሪውን እንደማይቀበሉት ያስታወቁ ሲሆን ይህንን የሰሙት ትራመፕ “በፈረንሳይ ወይን እና ሻምፓኝ ምርቶች ላይ የ200 በመቶ ታሪፍ (ቀረጥ) ስጥል ይቀበላል” ሲሉ ዝቷል።

ትራምፕ በዚሁ ሳምንት በሚካሄደው የዳቮስ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ላይ፣ ግሪንላንድን ከአውሮፓዊቷ ሀገር ዴንማርክ ስለመግዛት እንደሚወያዩም አረጋግጠዋል።

“ይህንን ማድረግ አለብን (መግዛት አለብን)፤ እነሱም ይህን ጉዳይ መፈጸም አለባቸው። ዴንማርኮች ድንቅ ህዝቦች ናቸው፣ ነገር ግን ግሪንላንድን መጠበቅ አይችሉም።

መሪዎቻቸውን አውቃቸዋለሁ፣ በጣም ጥሩ ሰዎች ናቸው፣ ነገር ግን እዛ (ግሪንላንድ) አይሄዱም” ሲሉ ትራምፕ አወዛጋቢውን የግዛት ግዢ ሃሳብ በድጋሚ አንስተዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates