ማህበራዊ
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 142 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 12/05/2018፡- በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 142 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ተብሏል፡፡
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 11 ዙር በረራ የተመለሱት 2 ሺህ 980 ወንዶች እና 141 ሴቶች እንዲሁም 21 ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 82 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ/ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 41 ሺህ 671 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል ሲል የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር መረጃ አሳይቷል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።



