አፍሪካ

የአፍሪካ ኅብረት በሶማሊያ ባካሄደው ዘመቻ ከ30 በላይ የአል ሸባብ ታጣቂዎች ተገደሉ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 08/04/2018፡- የአፍሪካ ኅብረት በደቡብ ሶማሊያ ሐሙስ ዕለት ባካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ከ30 በላይ የአልሸባብ ተዋጊዎች መገደላቸው ተገለፀ።

በታችኛው ሸበሌ ክልል የተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻው በአየር ኃይል የታገዘ እንደነበር የገለፀው ኅብረቱ፣ የሶማሊያ ጦር እና የአፍሪካ ኅብረት ወታደሮች በጋራ መሳተፋቸውን ገልጿል።

አፍሪካ ኅብረት ባወጣው መግለጫ በቅርቡ ከጌንዴርሼ እና ጂሊብ ማርካ የባሕር ዳርቻ አካባቢዎች ተገፍተው እንዲወጡ የተደረጉ ታጣቂዎች በወታደሮቹ ላይ ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ እርምጃ መወሰዱን ተናግሯል።

“በምድር እና በአየር በጥምረት በተፈጸመ ዘመቻ ከ30 በላይ የአልሸባብ ወታደሮች ሲደመሰሱ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል።”

በዘመቻው የሶማሊያ መከላከያ ወታደሮች፣ የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም)፣ የቀጠናዊ እና ዓለም አቀፍ አጋሮች እንዲሁም የኡጋንዳ ጦር ተሳትፈዋል።

አፍሪካ ኅብረት አክሎም ለጸጥታ አካላት እና ለሰላማዊ ዜጎች ስጋት የሆኑትን ለማስወገድ ፈጣን እርምጃ መውሰዱን ገልጾ ተልዕኮው ሰላማዊ ዜጎችን መከላከል እና የሰብዓዊ ድጋፍ ደህንነቱ በተጠበቁ መንገድ እንዲደርስ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል።

አልሸባብ የሶማሊያ መንግሥትን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሲዋጋ የነበረ ሲሆን አፍሪካ ኅብረት ወሰድኩት ባለው እርምጃ ላይ ያለው ነገር የለም።

አፍሪካ ኅብርት የአልሸባብን እንቅስቃሴ ለመገደብ እና በሶማሊያ ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋት እና ደህንነት እንዲኖር ለማድረግ በጋራ የሚሠራቸውን ሥራዎች እንደሚቀጥል ገልጿል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates