የተለያዩ
የኖቤል ሰላም ሽልማት ሜዳሊያ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተበረከተ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 08/04/2018፡- የቬንዙዌላ ተቃዋሚ መሪ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ የኖቤል የሰላም ሽልማት ሜዳሊያቸውን ለአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማበርከታቸውን ቢቢሲ ዘገበ።
የቬንዙዌላ ተቃዋሚ መሪ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በዋይት ሀውስ ባደረጉት ስብሰባ ላይ ሜዳሊያውን የሰጡት ትራምፕ ለቬንዙዌላ ነፃነት ለከፈሉት ዋጋ ዕውቅና ለመስጠት መሆኑን ገልጸዋል።
የአሜሪካ ወታደሮች በካራካስ የቬንዙዌላውን ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን በቁጥጥር ሥር ካዋሉ በኋላ ትራምፕን ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኟቸው ማሪያ ኮሪና ማቻዶ ዕለቱን ለቬንዙዌላውያን “ታሪካዊ ቀን” ሲሉ ጠርተውታል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ባስተላለፉት መልዕክት ምስጋናቸውን ገልጸው፤ ድርጊቱ አስደናቂ የጋራ መከባበር ምልክት መሆኑን ተናግረዋል።
የኖቤል ኮሚቴው በበኩሉ ሽልማቱ አንዴ ከተሰጠ በኋላ ሊሻር፣ ሊጋራ ወይም ለሌላ ሊተላለፍ የማይችል መሆኑን አስታውቋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኖቤል ሰላም ሽልማትን ለመሸለም ያላቸውን ፍላጎት በተደጋጋሚ ሲገልጹ መቆየታቸው በዘገባው ተመላክቷል።



