አውሮፓ
በጀርመን ጩቤ ይዞ ዝርፊያ ለመፈፀም የሞከረው ኤርትራዊ በፖሊስ ሽጉጥ ተመታ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 08/04/2018፡- ድርጊቱ የተፈፀመው በጀርመን ባደን ውተርበንግ ግዛት በሚገኘው ኡልም ከተማ ነው፡፡
በከተማው ውስጥ ብሉቦየር በተሰኘው አውራጎዳና አቅራቢያ ሚዲያ ማርኬት የተባለው ትልቅ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሸጫ መደብር ይገኛል፡፡
ቢልድ ጋዜጣ እንደዘገበው የ29 አመቱ ኤርትራዊ ትላንት ሮብ በአካባቢው ሰአት አቆጣጠር 12፡30 ፒኤም ላይ ጩቤ በመያዝ ይገባል፡፡
ነገሩ ያላማራቸው የመደብሩ ሰራተኞችም ‹‹በሩን ዝጉት›› እያሉ መጯጯህ ይጀምራሉ፡፡
ይህንን ጊዜ ተጠርጣሪው በያዘው ጩቤ ሁለት ሰራተኞችን ይወጋና ከመደብሩ ወጥቶ መሄድ ይጀመራል፡፡
እንደዘገባው ፖሊሶች በፍጥነት ወደስፍራው ደርሰው ይከታተሉትና ይደርሱበታል፡፡ ከዚያም የያዘውን መሳሪያ እንዲጥል ቢጠይቁትም ፈቃደኛ ሳይሆን ይቀራል፡፡
ከዚህም አልፎ የፖሊስ አባላትን በጩቤው ማስፈራራት በመቀጠሉ እንደተተኮሰበት ተገልጿል፡፡
ይህ ኤርትራዊ በፖሊስ የደረሰበትን ይህንን ጉዳት ተከትሎ ወደሆስፒታል የተወሰደ ሲሆን አሁን በፅኑ ህሙማን ክፍል ይገኛል፡፡
ጋዜጣው እንዳለው የመትረፍ እድሉ በጣም አነስተኛ መሆኑን ዶክተሮቹ ተናግረዋል፡፡



