የኢ/ያ ብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሬድዋን ሑሴን ወደ ሶማሊያ እንዳቀኑ መረጃዎች አሳይተዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 06/04/2018፡- አቶ ሬድዋን ሁሴን ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃመድ ጋር በዝግ ስብሰባ ላይ እንደተወያዩ እና ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተላከው መልእክት እንዳስተላለፉላቸው ተዘግቧል። የመልእክቱ ዝርዝር መረጃ ግን እስካሁን አልተገለጸም።
ሁለቱም መንግስታት ስለ ጉብኝቱ ዓላማ በይፋ አስተያየት ባይሰጡም፣ ውይይቱ በአካባቢያዊ ተለዋዋጭነት፣ በደህንነት ትብብር እና በአፍሪካ ቀንድ ላይ በተከሰቱ የቅርብ ጊዜ የጂኦፖሊቲካል እድገቶች ላይ ያተኮረ ሊሆን እንደሚችል ምንጮች ይጠቁማሉ።
በተለይ ሶማሊያ ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የነበራትን ስምምነት እንዲቋረጥ ማድረግዋ ተከትሎ በሁለቱም አገሮች የተፈጠረውን ክፍተት ለመሸምገል ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳሳየች መረጃዎች አመላክተዋል፡፡
አቶ ሬድዋን ሁሴን ከፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ በተጨማሪ ከሶማሊያው የደህንነት ሐላፊ መህድ ሳላድ ጋርም መወያየታቸው የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ጉብኝቱ የተደረገው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እሁድ እለት ወደ ጅቡቲ ከተጓዙ በኋላ በኤክስ ላይ በለጠፈው መረጃ፣ ውይይቱ በቀጠናዊ የጂኦፖሊቲካዊ እድገቶች፣ በሰላም እና ደህንነት እንዲሁም በተለይም በንግድ፣ በሎጂስቲክስ እና በልማት ላይ የጋራ ቁርጠኝነትን በማጠናከር ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልፀዋል።
አሁን ደግሞ የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተሩ ወደ ሞቃድሾ በማምራት ወይይት አድርገዋል፡፡
ይህ እርምጃ በአፍሪካ ቀንድ የዲፕሎማሲያዊ ምላሽን ያስከተለ ነው የተባለ ሲሆን የሶማሊያ መንግሥትም ሆነ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የደህንነት ኃላፊው ወደ ሞቃዲሾ ስላደረጉት ጉዞ ወይም ከሶማሊያ መሪዎች ጋር ስለተደረገው ውይይት ፍሬ ነገር ይፋዊ መግለጫ አልሰጡም።



