ኢኮኖሚ

በትግራይ ያጋጠመው የነዳጅ እጥረት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠው ተጠየቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 06/04/2018፡- የትግራይ ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ በትግራይ ውስጥ ለሚታየው አሳሳቢ የነዳጅ እጥረት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።

የነዳጅ አቅርቦት መጠን ከ12 ሚሊዮን ሊትር ወደ 850,000 ሊትር ቀንሷል ብለዋል ኢጀንሲው።

ኤጀንሲው ይህንን የተናገረው በዚህ ረገድ ለፌደራል መንግስት ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እያቀረበ መሆኑን በደብዳቤ ባሳወቀበት ወቅት ነው።

የትግራይ ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ ችግሩን ለመፍታት ላቀረባቸው ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ባለማግኘቱ ክልሉ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት እያጋጠመው መሆኑን ተናግሯል።

እንደ ትግራይ ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ ገለጻ፣ እስከ የካቲት 2017 ዓ.ም ድረስ 12 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ወደ ትግራይ ይገባ እንደነበር ያስታወሰው ኤጀንሲው ከየካቲት ወር በኃላ የነዳጅ አቅርቦቱ በከፍተኛ በመቀነሱ ለሰብአዊ ድጋፎች ማጋጋዣ፣ ለህዝብ መጋጋዣ፣ ለኢንዳስትሪ እና ኢንቨስትመንት ይውል የነበረው ነዳጅ ለነብሲ አድን ብቻ ታጥሮ ቀርተዋል ብለዋል።

የትግራይ ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ በታህሳስ ወር 850,000 ሊትር ነዳጅ ብቻ መቅረቡን ለፌዴራል የንግድና ቀጠናዊ ውህደት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡፤

በነዳጅ እጥረት ምክንያት ለተከሰቱት ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ ከሌለ፣ መንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ አገልግሎቶች፤ መደበኛና ድንገተኛ የሕክምና አገልግሎቶችንና ድንገተኛ የሰብዓዊ እርዳታ ሥራዎችን  ችግር ውስጥ እንደሚገቡ በመግለፅ የፌደራል መንግስት ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates