ኢትዮጵያ

የብሄራዊ ምክክር ኮሚሽን ከህወሓት አመራሮች ሶስት ጊዜ ተገናኝቶ መወያየቱን አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 06/04/2018፡- የምክክር ኮሚሽኑ ሰሙኑን በጅማ ከተማ ከባለ ድርሻ ኣካላት ባደረገው ውይይት በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከተሰረዘው የህወሓት አመራሮች ሶስት ጊዜ ተገናኝቶ እንደተወያየ እና አመራሮቹም ደስተኞች እንደነበሩ ገልፀዋል፡፡

‘’በቢሮአቸው ሶስት ጊዜ አግኝተን ተወያይተናል‘’ ያላቸው የህወሓት አመራሮች እነማን መሆናቸው ያልጠቀሱት ከኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ዮናስ አዳዬ የህወሓት አመራሮች ‘’አንዳንድ መመለስ ያለባቸው ጥያቄዎች ቢኖሩንም በምክክሩ ደስተኞች ነኝ‘’ ብሎን ነበር፤ አሁን እያገኘናቸው እየተነጋገርን ነው ብለዋል፡፡

ትግራይን ያላካተተ ሃገራዊ ምክክር ሙሉ አይሆንም የሚል የፀና አቋም አለን ያሉት ኮሚሽነሩ ይህን የምናገረው እንደ ዮናስ ሳይሆን እንደኮሚሽኑ ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የህወሓት አመራሮች ባገኘናቸው ጊዜ አንድም ቀን አንፈልጋችሁም የሚል ምላሽ አልሰጥኑም የሚሉት ኮሚሽነሩ አንዳንድ መመለስ የሚገባቸው ነገሮች አሉን የሉዋቸው ነገሮች ምንምን እንደሆኑ ግና በዝዝር አላብራሩም፡፡

በአሁን ጊዜ በትግራይ ክልል ብቻ አጀንዳ መለየት ስራዎች እንዳልሰራ ሚገልፀው ኮሚሽኑ በትግራይ በኩል ደግሞ በምክክሩ ለመሳተፍ መጀመሪያ ትግራይ ከጦርነቱ በፊት ወደነበረችበት ትመለስ የሚል ቅድመ ሁኔታ ሲነሳ ይሰማል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates