አፍሪካ

ሶማሊላንድ የፌዴራል መንግሥት ውሳኔን ውድቅ አደረገች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 06/04/2018፡- የሶማሊላንድ ባለሥልጣናት የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት የወሰነውን ውሳኔ “አስፈላጊ ያልሆነ” ሲሉ ውድቅ ያደረጉት ሲሆኑ ግዛታቸውን በራሳቸው እንደሚያስተዳድሩ እና የበርበራ ወደብን ሙሉ በሙሉ እንደሚቆጣጠሩ አረጋግጠዋል።

በሶማሊላንድ የሚገኙ ባለሥልጣናት ግዛቲቱ ራስዋን የቻለች አገር ሆና የራስዋን ጉዳዮች እንደምታስተዳድር ተናግረዋል፡፡

በሞቃዲሾ የሚደረጉ ውሳኔዎች በሶማሊላንድ አስተዳደር ወይም በአሠራሩ ላይ ምንም ተጽእኖ እንደሌላቸው አፅንዖት ሰጥተዋል።

ፑንትላንድ እና ጁባላንድም ተመሳሳይ ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል ቱርክ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት እና በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መካከል ስላለው ውጥረት ነገ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ አቡ ዳቢ እንደሚጓዙ የአናዶሉ ዘገባ አመልክተዋል፡፡

አንካራ ከሞቃዲሾ በጣም ንቁ አጋሮች አንዷ እንደመሆኗ መጠን፣ ቱርክ የፌዴራል መንግሥትን፣ የፑንትላንድ፣ የጁባላንድ እና የሶማሌላንድን የፖለቲካ አለመግባባቶችን ተከትሎ የአቡ ዳቢን ስጋቶች ለማቃለል መርዳት ትችል እንደሆነ ጥያቄዎች እየጨመሩ ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates