አፍሪካ

የፑንትላንድ እና ጁባላንድ አስተዳደሮች የሶማሊያ ካቢኔ የኢሚሬትስ ስምምነት መሰረዙን ተቃወሙ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/04/2018፡- የጁባላንድ ግዛት ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጋር የተደረጉ ስምምነቶችን የሻረ የፌዴራል ካቢኔ ውሳኔን ውድቅ አድርጓል።

የኪስማዮ የወደብ ስምምነትን ጨምሮ የሰረዘው የሶማሊያ ካቢኔ የጁባላንድ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ የተቃወሞው ሲሆን፣ የሶማሊያ ጊዜያዊ ሕገ መንግሥት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በመሠረተ ልማት ስምምነቶች ላይ ሥልጣን እንደሚሰጡት ገልጾ፣ እንደዚህ ያሉ ስምምነቶችን የማሻሻል ወይም የመሰረዝ መብት ያላት ጁባላንድ ብቻ እንደሆነች አሰገንዝቧል።

በተመሳሳይ የፑንትላንድ አስተዳደርም ውሳኔው በመቃወም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ስምምነቶች ሕጋዊ እና የማይነኩ ናቸው ብሏል።

የፑንትላንድ መንግስት የሶማሊያ የፌዴራል ካቢኔ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር ያደረጋቸውን ስምምነቶች ለመሰረዝ ያደረገውን ሙከራ ውድቅ በማድረግ፣ ሞቃዲሾ ጣልቃ የመግባት ህጋዊ ስልጣን እንደሌላት ገልጿል።

የፑንትላንድ አስተዳደር ባወጣው ግልጽ መግለጫ፣ ከኢሚሬትስ ጋር የተደረገው የቦሳሶ የወደብ ልማት እና የደህንነት ትብብር ስምምነቶች በሕገ መንግሥታዊ ሥልጣናቸው ስር እንደሚወድቁ ተናግሯል።

ባለስልጣናቱ የፑንትላንድ ሕገ መንግሥትን እና የሶማሊያ የ2012 ጊዜያዊ የፌዴራል ሕገ መንግሥት አንቀጽ 142ን ጠቅሰው የፌዴራል ካቢኔ ውሳኔ “ውድቅ እና የማይፀና” በማለት አውጀዋል። የሶማሊያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውይይት ካደረገ በኋላ ባወጣው መግለጫ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር የተፈረሙ ስምምነቶችን መሰረዙን ይፋ አድርጓል።

ይህም ከወደብ፣ ከደኅንነት እና ከመከላከያ ጋር የተያያዙ ስምምነቶችን ያካትታል።

ከበርበራ፣ ከቦሳሶ እና ከኪስማዮ ወደቦች ጋር የሚገናኙ ስምምነቶች እንዲሁም ከሶማሊያ የፌደራል እና ክልላዊ ተቋማት ጋር የተደረጉ ስምምነቶች ሁሉም ተሰርዘዋል ብሏል ካቢኔው።

ከውሳኔው በኃላ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከቦሳሶ የጦር ሰራዊቷን ያስወጣች ስትሆን ከብዙ የሶማሊያ ሰፈሮች የሃርድዌር እና የሰራተኞችን አባላት እያስወጣች መሆኑን ታውቋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates