ኢኮኖሚ

የትራምፕ አስተዳደር ከኢራን ጋር በሚገበያዩ አገራት ላይ 25% ታሪፍ መጣሉን አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/04/2018፡- የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚገበያዩ አገራት ላይ 25% ታሪፍ መጣላቸውን አስታወቁ።

ከኢራን ጋር የንግድ ትስስር ያላቸው አገራት ላይ የተጣለው ታሪፍ የቴህራን መንግሥት ላይ ጫና ለማሳደር ያለመ ነው ተብሏል።

ትራምፕ ከኢራን ጋር “የሚገበያዩ” አገራት ላይ “በአፋጣኝ የሚተገበር” ታሪፍ መጣላቸውን ቢገልጹም ዝርዝር መረጃ ግን አልሰጡም።

ቻይና የኢራን ዋነኛ የንግድ አጋር ስትሆን ኢራቅ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ቱርክ እና ሕንድም ከኢራን ጋር የንግድ ትስስር ያላቸው አገሮች ናቸው።

“ከኢራን ጋር የሚገበያይ ማንኛውም አገር ከአሜሪካ ጋር በሚያደርገው የንግድ ልውውጥ ላይ 25% ታሪፍ ይጣልበታል” ብለዋል ትራምፕ።

ታሪፍ የተጣለባቸው አገራት የትኞቹ እንደሆኑ ግን በዝርዝር አልተገለጸም።

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ካሮላይን ሌቪት ኢራን ላይ የአየር ጥቃት ማድረስን ጨምሮ ሌሎችም ወታደራዊ አማራጮች እንዳሉ ተናግረዋል።

የኢራን መገበያያ ገንዘብ ሊያል ከአሜሪካ ዶላር አንጻር ምንዛሬው መዋዠቁን በመቃወም በቴህራን የባዛር ነጋዴዎች የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ በተለያዩ ከተሞች የቀጠለ ሲሆን አሜሪካና እስራኤል ተቃውሞውን በማቀጣጠል በኢራን ተከሷል።

የአሜሪካው የመብት ተሟጋች ‘ሂውማን ራይትስ አክቲቪስት ኒውስ ኤጀንሲ’፤ 500 ተቃዋሚዎች እና 48 የፀጥታ ባልደረቦች መሞታቸውን ማረጋገጡን ያስታወቀ ሲሆን ለቀናት ኢንተርኔት በመቋረጡ ከኢራን የሚወጡ መረጃዎችን ማረጋገጥ አለመቻሉ እየተገለፀ ይገኛል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates