ፖለቲካ

የኤርትራ ቀይ ባህር ዓፋር ህዝቦች ራስን በራስን የማስተዳደር መብት ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ በኤርትራ የዓፋር ህዝቦች ተቃዋሚ ሐይሎች አስታወቁ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/04/2018፡- ተቃዋሚ ሐይሎቹ በኢትዮጵያ ዓፋር ክልል ሰመራ ከተማ ባካሄዱት የጋራ ኮንፈረንስ የተለያዩ ውሳኔዎች አሳልፏል።

“ለፍትህ ዴሞክራሲያዊ አገዛዝ እና የአምባገነንነት ፍጻሜ” በሚል በተካሄደው ኮንፈረንስ የቀይ ባህር ዓፋር ዴሞክራሲያዊ ግንባር እና የኤርትራ ዓፋር ብሄራዊ ኮንግረንስ የቀይ ባህር ዓፋር ህዝቦች የራስ ዕድል በራስ የመወሰን መብት ለማረጋገጥ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው አስታውቋል።

ሁለቱም ድርጅቶች የኤርትራ ቀይ ባህር አፋር ህዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት፣ በአለም አቀፍ ህጎች እና በአህጉራዊ ቻርተሮች የተረጋገጠ እና የማይናወጥ የፖለቲካ ህጋዊ መብት መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህም የኤርትራ ቀይ ባህር አፋር ህዝቦች ትግል ነፃነትን፣ እኩልነትን እና ሰብአዊ ክብርን የሚያረጋግጥ ፍትሃዊ ዴሞክራሲያዊ አገዛዝ ለማቋቋም ያለመ መሆኑን እና ለአስርተ ዓመታት የተገለለ እና አምባገነንነትን የሚያስቆም መሆኑን ሁለቱም ድርጅቶች በሰጡት የጋራ መግለጫ አረጋግጧል። የኤርትራ ህዝባዊ ግንባር (ህግደፍ) የጋራ ጠላት ነው ያሉት ሁለቱ ድርጅቶች አምባገነናዊ አገዛዙ በዳንካሊያ እና በክልሉ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የኤርትራ አፋሮች የጋራ ጠላት እንደሆነም አስታውቀዋል።

ይህ ስርዓት ስጋቱ ለኤርትራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ለሚፈጠረው አለመረጋጋት እና ዘላቂ ውጥረት ዋና ምንጭ እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠራል በማለትም ግጭቶችን በማቀጣጠል እና ቀጠናዊ ሰላም እና ልማት እድሎችን በማደናቀፍ ቀጥተኛ ተጠያቂ ነው ብሏል።

ስርዓቱን ለመገልበጥ የሁሉም አይነት የትግል ዓይነቶች እንደሚጠቀሙ ያረጋገጡት ድርጅቶቹ አምባገነንነትን መቋቋም በአለም አቀፍ ህጎች የተረጋገጠ ተፈጥሯዊ መብት መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም የትጥቅ ትግል በኤርትራ ውስጥ ያለውን ጨቋኝ ሰርዓት ለማስወገድና የቀይ ባህር አፋሮችን መብት ለመከላከል፣ ጭቆናን ለማስወገድ ካሉት አማራጮች አንዱ እንደሆነ ማረጋገጥ እንወዳለን ብሏል ድርጅቶቹ።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates