የተለያዩ

በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ ወደ 8000 የሚጠጉ ሠዎች በቁጥጥር ስራ መዋላቸውን የአፋር ክልል ፖሊስ አስታውቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/04/2018፡- ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በህገ-ወጥ ደላሎች ተታለው በተለያዩ የዝውውር መስመሮች ላይ ሲጓዙ የነበሩ ከ7,900 በላይ ዜጎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ቢልኤ አህመድ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ የክልሉ ፖሊስ ከመደበኛ የጸጥታ ስራው ባሻገር ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰው ሃይል በመመደብ በየፍተሻ ጣቢያዎቹና በመተላለፊያ መስመሮች ላይ ተከታታይነት ያለው የክትትል ስራ እያከናወነ ይገኛል።

እንደ ኮሚሽነሩ ማብራሪያ ከሆነ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎችን የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በራሱ የትራንስፖርት ወጪና በአባላቱ አጃቢነት ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ መጡባቸው አካባቢዎች እንዲመለሱ ተደርጓል።

እነዚህ ተመላሽ ዜጎች ኮምቦልቻ፣ አላማጣ፣ መቀሌ፣ ከሚሴ፣ አዳማ እና ሀረርጌ ወደመሳሰሉ መነሻ አካባቢያቸው እንዲቀላቀሉ የተደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

ይሁን እንጂ የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል መነሻዎች ከአፋር ክልል ውጪ መሆናቸው ለቁጥጥር ስራው ትልቅ ፈተና እንደሆነባቸው ኮሚሽነር ቢልኤ አህመድ አብራርተዋል።

አብዛኛው ተጓዦች ከአጎራባች ክልሎች ማለትም ከአማራ፣ ከትግራይ እና ከኦሮሚያ ክልሎች የሚነሱ በመሆናቸውና ደላሎቹም የሚንቀሳቀሱት በእነዚሁ አካባቢዎች በመሆኑ ወንጀሉን ከምንጩ ለማድረቅ አዳጋች ሆኗል ተብሏል።

ከሁለት ቀናት በፊት ወደ 100 የሚጠጉ በተሳቢ መኪና ተጭነው ሲጓዙ የነበሩት ሕገ ወጥ ስደተኞች በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ አደባባይ ባጋጠመ አደጋ 22 መሞታቸው እና 35 ከባድ አደጋ እንዳጋጠማቸው መዘገባችን ይታወሳል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates