ፖለቲካ
ሶማሊያ ሶማሊላንድን ለመቆጣጠር እየተዘጋጀች መሆኗ ገለፀች።

ኢትዮ ሞኒተር፡- 27/04/2018፡- የሶማሊያ አስተዳደር በኤደን ባሕረ ሰላጤ ውስጥ የእስራኤል ወታደራዊ ሰፈርን ለመከላከል ሶማሊላንድን ለመውረር እየተዘጋጀች መሆኗ ተሰማ።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ከአል-አረቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በሶማሊላንድ ላይ ለሚወሰደው ወታደራዊ እርምጃ በንቃት እየተገመገመ መሆኑን አምነዋል።
እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና ከሰጠተች በኋላ የውጭ መንግስታት ሞቃድሾ ከላስአኖድ ወደ ሶማሊላንድ ጥቃት ልትሰነዝር እንደምትችህ ስያሳስቡ ቆይቷል።
ላሳአኖድ ከዚህ በፊት ምንም አይነት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያልነበረው ቦታ እና በሚሊሻ ቁጥጥር ስር የነበረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ በኃላ ግን የሶማሊያ ሰራዊት መንቀሳቀስ እንደጀመረበት ተገልጿል።
ከዚህ በመነሳትም ሶማሊያ በሶማሊላንድ ጥቃት ልትሰነዝር እንረደምትችል ተገምቷል።



