የተለያዩ
የአውሮፓውያኑ አዲሱ ዓመት በመላው ዓለም በድምቀት ተከበረ

ኢትዮ ሞኒተር፡ 23/04/2018፡- አዲሱ የአውሮፓውያኑ ዓመት 2026 በመላው ዓለም በድምቀት ተከብሯል።
ከኬንያ መዲና ናይሮቢ እስከ አሜሪካዋ ግዙፏ ከተማ ኒው ዮርክ እንዲሁም ለንደን እና ሲድኒ አዲሱን ዓመት እኩል ለሊት በድምቀት ተቀብለዋል።
2026ን ቀድመው ከተቀበሉ ክፍለ ዓለማት መካከል የፓሲፊክ ውቅያኖስ ሀገራት እንዲሁም ኒውዚላንድ እና አውስትራሊያ ይጠቀሳሉ።
በለንደን ቢግ ቤን የተሰኘው ታዋቂ ደወል አዲሱን ዓመት አስመልክቶ ሲቃጭል ተሰምቷል።
በቴምስ ወንዝ ዙሪያ ደግሞ 12 ሺህ ገደማ ርችቶች ተተኩሰዋል።
በስኮትላንድ ዋና ከተማ ኤደንብራም እንዲሁ በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾች በተገኙበት ደማቅ ርችት ተተኩሷል።
የጀርመኗ በርሊን፣ የስፔኗ ባርሴሎና፣ የፈረንሷይዋ ፓሪስ ሌሎች አዲሱን ዓመት በድምቀት የተቀበሉ ከተማዎች ናቸው።
ግሪንላንድ፣ ብራዚል እና ኒው ዮርክ ከተቀረው ዓለም ዘግይተው አዲሱን ዓመት ተቀብለዋል።



