ዲፕሎማሲ
ጂቡቲ የሶማሊላንድ ዲፕሎማቲክ ቢሮን ዘግታ ዲፕሎማቶቿ መጥራትዋ ተሰማ፡፡
በተመሳሳይ ሶማሊላንድም ዲፕሎማቶቿ ከጅቡቲ ወደ ሃርጌሳ መጥራትዋ ታውቀዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 23/04/2018፡- እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷን ተከትሎ ከሐርጌሳ ጋር ውጥረት ውስጥ የገባችው ጅቡቲ፤ የሶማሊላንድ ዲፕሎማቲክ ቢሮን እንደዘጋች እና ዲፕሎማቶቿን ከሀርጌሳ መልሳ እንደጠራች አንድ የአገሪቱ መንግሥት ባለስልጣን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የሶማሊላንድ ባለስልጣን በበኩላቸው ሐርጌሳም በተመሳሳይ በጅቡቲ የሚገኙ ዲፕሎማቶቿን ለምክክር እንደጠራች ተናግረዋል።
የአሁኑ ሁኔታ እስራኤል ለሶማሊላንድን የአገርነት እውቅና ከሰጠችበት ጊዜ አንስቶ የሁለቱ ተጎራባቾች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እጅግ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መውረዱን ያሳያል።
ይህ ዲፕሎማሲያዊ መቃቃር በተለይም ለዓለም አቀፍ ጉዞ የጂቡቲ ፓስፖርትን በሚጠቀሙ የሶማሊላንድ ባለሥልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች፣ በተለይም በሶማሊላንድ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ጉዞ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ይጠበቃል።
እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷን በፅኑ ከተቃወሙ የሶማሊያ ጎረቤቶች መካከል ጂቡቲ አንዷ ናት።



