ማህበራዊ

በአማራ ክልል በሚገኝ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ አንድ ኤርትራዊ በታጣቂዎች መገደሉን ተከትሎ የኤርትራ ስደተኞች ሰልፍ ወጡ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 23/04/2018፡- እስካሁን ድረስ 11 የኤርትራ ስደተኞች እንደተገደሉ እና የዓለም ማህበረሰብ እንዲደርስላቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

ከ15 ዓመታት በላይ ጥገኝነት ሲጠይቅ የቆየ የ52 ዓመት ኤርትራዊ፣ የሶስት ልጆች አባት፣ ታህሳስ 20 ቀን 2018 ዓ/ም በአለምዋጭ የስደተኞች ካምፕ በታጣቂዎች መገደሉ ተሰምተዋል።

በአለምዋጭ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የኤርትራውያን ስደተኞች ስቃይ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው የሚሉት ስደተኞቹ ሰሚ የለንም፤ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድርጅቶች የሉም፤ ወደ ሆስፒታል ስንሄድ ህክምና ሳይሆን አስከሬን ተሸክመን ነው የምንመለሰው በማለት እስካሁን አስራ አንድ ሰዎች መቅበራቸው አስታውቀዋል፡፡

አለምዋጭ በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ የሚገኝ የስደተኞች ካምፕ ሲሆን ስደተኞቹ በትግራይ ጦርነት ወቅት ለዓመታት ተጠልለው ከነበሩበት ከማይ ዓይኒ እና ዓዲ ሓሩሽ የስደተኞች ካምፖች ወደ አማራ ክልል የተዘዋወሩ ናቸው።

የኤርትራ ጦር ማዕከላቱን በማውደሙ በሦስት የስደተኞች ካምፖች ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያንን እንዲበተኑ ያደረገ ሲሆን በወቅቱ በተዘገበው ዘገባ መሠረት ወደ 20,000 የሚጠጉ ስደተኞች በግዳጅ ወደ ኤርትራ እንዲመለሱ አድርጓቸዋል።

የተቀሩት ስደተኞች በአማራ ክልል በሚገኘው የአለምዋጭ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ በቂ ሰብዓዊ እርዳታ እና ትኩረት ሳይደረግላቸው አየኖሩ እንደሆኑ በመግለፅ ማንነታቸው በማይታወቁ ታጣቂዎች እየተገደሉ፣ እየታፈኑ እና ፆታዊ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ በሰልፉ አስታውቃዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates