ዲፕሎማሲ

የኤርትራው መሪ ኢሳይያስ አፈወርቂ እሥራኤል ለሶማሊላንድ ዕውቅና መስጠቷን መኮነናቸውን ተከትሎ ሶማሊላንዶች ኤርትራ 34 ዓመት ሙሉ በአንድ አምባገነን የምትመራ ሀገር በማለት ተቸዋቸው፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 22/04/2018፡- ሶማሊላንድ እ.አ.አ. ከ1991 ጀምሮ ላለፉት 34 ዓመታት 6 ፕሬዝዳንቶች እንደቀያየረች ያስተወሱት ሶማሊላንዳዊያን ኤርትታ ግን በእነዚህ ዓመታት በአንድ ፕሬዝዳንት ብቻ እንደተመራች በመግለፅ በሁለቱም አገሮች ያለውን የዴሞክራሲ ልዩነት አሳይተዋል፡፡

በሶማሊላንድ 15 የግል ባንኮች እንዳልዋት የሚጠቁመው መረጃው በኤርትራ ግን አንድ የመንግስት ብቻ እንዳለ፤ በሶማሊላንድ 5G ሲኖር በኤርትራ ግን ኢንተርኔት የሚባል ነገር እንደሌለ አመላክተዋል፡፡

እንዲሁም በሁለቱም አገሮች ያሉት ወደቦች በማነፃፀር የበርበራ ወደብ በዓመት 1.5 ሚሊዮን ቶን ሲንቀሳቀስበት የአሰብ ወደብ ግን በዓመት 150 ሺ ቶን ብቻ እንደሚያስተናግድ ልዩነቱን አስቀምጠዋል፡፡

በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ የተበሳጩት ሶማሊላንዳዊያን በኤርትራ ፓርላማ እና የኒቨርሲቲ የሚባል ነገር እንደሌለ ሶማሊላንድ ውስጥ ግን ፓርላማ ከመኖሩም ባለፈ 7 የመንግስትንና 35 የግል በድምሩ 42 ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

የኤርትራ መንግስት እስራኤል ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና መስጠቱ ተከትሎ ከመቃወሙም በላይ ቻይና በታይዋን ያላትን ተመሳሳይ ስጋት ተጠቕማ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ጠንካራ አቋም እንድትይዝ አነሳስታለች፡፡

በዚህ የተቖጡ ሶማሊላንዳዊያን ኤርትራ እና ሶማሊላንድ በሁሉም ነገር ሰማይ እና መሬት ልዩነት እንዳላቸው በአሃዛዊ መረጃዎች ተጠቅሞ እያሳዩ ይገኛሉ፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates