ኤስያ

ታይዋን፣ እስራኤል ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና ለመስጠት ያስተላለፈችውን ውሳኔ በአዎንታ መቀበሏን አስታወቀች፡፡

ታይዋን፣ እስራኤል እና ሶማሊላንድ የዴሞክራሲ አገሮች ናቸው ስትልም ገልፃለች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 21/04/2018፡- የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የእስራኤልን እርምጃ በማድነቅ፤ ታይዋን፣ እስራኤል እና ሶማሊላንድ “የዲሞክራሲ፣ የነፃነት እና የህግ የበላይነት እሴቶችን የሚጋሩ ተመሳሳይ አመለካከት ያላቸው ዲሞክራሲያዊ አጋሮች ናቸው” ሲል ገልጿል።

በተጨማሪም ውሳኔው በታይዋን፣ በእስራኤል እና በሶማሊላንድ መካከል በሁሉም መስኮች የጠበቀ የሶስትዮሽ ትብብር እንዲኖር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል ብሏል።

ቀደም ሲል እ.አ.አ. ነሐሴ 2020 ታይዋን በሶማሊላንድ መዲና ሀርጌሳ ተወካይ ጽሕፈት ቤት የከፈተች ሲሆን፤ ሶማሊላንድም በተመሳሳይ በዚያው ዓመት በታይዋን መዲና ታይፔ ጽሕፈት ቤቷን በመክፈት ምላሽ ሰጥታለች።

በቅርቡ በሐምሌ ወር ሁለቱ ወገኖች በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ ያለውን የአሰሳ ደኅንነት በጋራ ለመጠበቅ የየብስ ጠረፍ ላይ ጥበቃ ትብብራቸውን ለማጠናከር  ስምምነት መፈራረማቸውን ፎከስ ታይዋን በዘገባው አመልክቷል።

Show More

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates