አፍሪካ

የተባበሩት መንግስታት ግምጋሚ ቡድን ወደ ሱዳን ኤል ፋሸር እንደላከ አስታወቀ፡፡

ይህም ኤል ፋሻር በፈጣን ድጋፍ ሐይሉ እጅ ከወደቀች ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብለዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/04/2018፡- የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ድርጅት አስተባባሪ ፅ/ቤት(OCHA) በሰሜን ዳርፉር ኤል ፋሸር የግምገማ ቡድን ቅዳሜ ዕለት መድረሱን አስታውቋል።

ድርጅቱ እንዲህ አይነት ተልእኮ ሲልክ ከተማዋ ከወራት ከበባ እና ከባድ ውጊያ በፈጣን የድጋፍ ኃይሎች (RSF)ስር ከወደቀች ከተወረረች በኋላ የመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ መረጃዎች አሳይተዋል።

ኦቻ እንደገለጸው ጉብኝቱ “ሰፊ የሰብአዊ ድርድር”ን ተከትሎ የመጣ መሆኑን በመግለፅ ይህም ነዋሪዎች የእንስሳት መኖ እንዲበሉ ካስገደዳቸውን ወራትን የዘለቀ ከበባ በኋላ ነው ብለዋል።

የፈጣ ድጋፍ ሐይሉ ከተማዋን ጥቅምት 26 ከተቆጣጠረ በኃላ በርካታ ዜጎች መሰደዳቸው በመግለፅ የተቀሩት ደግሞ የጅምላ ግድያ ተፈፅሞባቸዋል ሲል ገልፀዋል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቡሎስ የተልእኮውን መምጣት በደስታ ተቀብሎ፣ በአሜሪካ የሚመራው የዲፕሎማሲ ጥረት ይህንን እንዳመቻቸላቸው ተናግረዋል።

“የተባበሩት መንግስታት የግምገማ ተልዕኮ በመጨረሻ ኤል ፋሸር መድረሱን ማየት አበረታች ነው” ሲሉ ቡሎስ የሰብአዊ ስምምነት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፣ የሱዳን ጦርም ሆነ የRSF ለሁሉም አካባቢዎች ያለምንም እንቅፋት የእርዳታ አቅርቦት እንዲፈቀዱም አሳስበዋል።

ታዊላ ተብሎ በሚጠራው የተፈናቃዮች መጠሊያ ማእከል ብቻ በአሁኑ ጊዜ ከ655,000 በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ እነዚህም አብዛኛዎቹ በኤል ፋሸር የተከሰተውን ሁከት የሸሹ መሆናቸው ተረጋግጠዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates