አፍሪካ

ቻይና በፀጥታው ምክር ቤት ከሶማሊያ ጋር እንድትቆም ኤርትራ ጠየቀች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/04/2018፡- የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በሶማሊላንድ ዕውቅና ጉዳይ ዛሬ [ሰኞ] በሚያደርገው ስብሰባው ላይ ቻይና የሶማሊያን ሉዓላዊነት እንድትከላከል ኤርትራ ጠየቀች።

ቻይና እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን ዕውቅና ከታይዋን ጋር በማመሳሰል ምክር ቤቱ “የማያወላውል ምላሽ እንዲሰጥ” የሚጠበቅባትን “የሞራል ኃላፊነት እንድትወጣ” ኤርትራ ጥሪ አቅርባለች።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ትላንት ባወጣው መግለጫ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው ዕውቅና “ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ አደገኛ ቀውስ እና ብጥብጥ ለመፍጠር ለረጅም ጊዜ ሲብላላ የቆየ ጉዳይ ነው” ብሎታል።

“ስለዚህም በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት እና በአባላቱ ደረጃ የማያሻማ ምላሽ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው” ብሏል መግለጫው።

“ከዚህ አንጻር ይህ ጉዳይ ከታይዋን ጉዳይ ጋር የሚመሳሰል በመሆኑ ቻይና ከምታራምደው አቋም አንጻር ያለባትን ሞራላዊ ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅባታል” ስትል ኤርትራ ቻይና በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ የሶማሊላንድን ዕውቅና የሚቃወም አቋም እንድታራምድ ጥሪ አቅርባለች።

ቻይና እስራኤል የሰጠችውን ዕውቅና ከተቃወሙ አገራት መካከል ስትሆን ኤርትራም የእስራኤልን እርምጃ ተቃውማለች።

ባለፉት ሦስት ቀናት ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኖ የቆየው እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው የአገርነት ዕውቅናን በተመለከተ ዛሬ ሰኞ ታኅሣሥ 20/2018 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ንግግር ይደረግበታል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates