መካከለኛ ምስራቅአፍሪካ

የአፍሪካ ህብረት እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን እውቅና አወገዘ፡፡

ለሶማሊያ “የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት” ያለኝን “ጽኑ ቁርጠኝነት” እወቁሉኝ ኣለ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 18/04/2018፡- የእስራኤል የሶማሊላንድ እውቅና ከአፍሪካ ህብረት እስከ አረብ ሊግ፣ ከአሜሪካ እስከ የአውሮፓ ህብረት ድረስ የመነጋገሪያ ነጥብ ሆኗል።

የሶማሊያ መንግስት የእስራኤልን ውሳኔ የሶማሊያን ሉዓላዊነት መዳፈርነ ነው ብሎታል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ሶማሊላንድን እንደ ነጻ ሀገር እውቅና ለመስጠት ማንኛውንም እርምጃ ውድቅ በማድረግ የአፍሪካ ህብረት ለሶማሊያ “አንድነት እና ሉዓላዊነት” ያለውን “ጽኑ ቁርጠኝነት” አረጋግጠዋል።

በሶማሊላንድ “በቅርብ ጊዜ በተከሰቱት ክስተቶች” ላይ መግለጫ የሰጡት፣ መሃመድ ዩሱፍ የአፍሪካ ህብረት “በህብረቱ ሕጎችና መርሆዎች ላይ በመመስረት ለረጅም ጊዜ የቆየውን እና ወጥ የሆነውን አቋሙን ያለምንም ጥርጥር ያረጋግጣል” ብለዋል።

እስራኤል ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ/ም ሶማሊላንድን እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር መሆነዋ ይፋ አድርጋለች፡፡

ለ30 ዓመታት ዓለም አቀፍ እውቅና ሳይኖራት ከሶማሊያ ተገልላ የቆየችው የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእስራኤል የአሀርነት እውቅና አግኝታለች።

እስራኤል እና የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ አምባሳደሮችን መሾም እና በሁለቱም ሀገራት ኤምባሲዎችን መክፈትን ጨምሮ ሙሉ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለመመስረት ስምምነት ተፈራርመዋል ሲሉ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዲዮን ሳር ተናግረዋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የሶማሊላንድ ሪፐብሊክን እንደ ነጻ እና ሉዓላዊ ሀገር በይፋ እውቅና በመስጠቷ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ የእስራኤልን ድርጊት ተቃውማለች፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም የእስራኤል የሶማሊላንድን እውቅና እንደማትደግፍ ተናግረዋል።

ትራምፕ እንደ ኔታንያሁ ሶማሊላንድን እውቅና ለመስጠት እንደማይቸኩሉ ተናግረዋል።

ሶማሊያ፣ ግብፅ፣ ቱርክ፣ ጅቡቲ፣ እስራኤል የሶማሊላንድን እውቅና አውግዘዋል።

የአራቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለሶማሊያ የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ሙሉ ድጋፍ እንዳላቸው ገልጸዋል።

በተለይ ቱርክ እስራኤል በሶማሊላንድ የወሰደችውን ውሳኔ በፍልስጤም ላይ የፈጸመችው የዓለም አቀፍ ህግ ጥሰት ቀጣይነት ነው ብላ ጠርታዋለች።

በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች የፍልስጤምን ዜግነትና ሉዓላዊነት በመካድ ጦርነት በማካሄድና የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈፀም የምትከሰሰው እስራኤል አሁን ሶማሊላንድን እውቅና መስጠትዋ ለህዝቦችን ነፃነት ተቆርቁራ ሳትሆን አሁን በጋዛና ዌስት ባንክ እየፈፀመችው ላለው የሕገ-ወጥ ሰፈራ አጀንዳ መቀየሪያ ነው በማለት የመካከለኛው ምስራቅና የምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ ተንታኞች እየወቀሱዋት ይገኛሉ።

እእዲሁም የአረብ ሊግ የእስራኤልን ውሳኔም በመግለጫ ያወገዘ ሲሆን የኢተዮጵያ እና የኤርትራ መንግስታት አቋም እስካሁን አይልታወቀም፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates