ኢኮኖሚ

የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት የፌደራልና የክልል መንግስታት ጥሪ አቀረቡ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 15/04/2018፡- ፕሬዝዳንቱ በትግራይ የተፈናቃዮች ካምፖች በረሃብ እየሞቱ ላሉት ዜጎች ለመታደግ ሁሉም ሰብአዊነት የሚሰማቸው አካላት ድጋፍ እንድያደርጉ ጥሪ አቅረበዋል፡፡

‘’ከሰሞኑ በክልላችን ሕፃፅ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣብያ ውስጥ ባሉ ወገኖች ላይ ያጋጠመውን የረሃብ አደጋ የሚያሳይ ቪድዮ ለህዝባቸው በሚቆረቆሩ ጥቂት ወጣቶች በመውጣቱ ምክንያት ባያችሁት እና በሰማችሁት ችግር አዝናችሁ ወገናችሁ የሆነውን የተፈናቀለ ህዝብ ለመርዳት እያደረጋችሁ ላለው ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል ታደሰ ወረደ፡፡

በተለይ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትኖሩ ወጣት ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ኤርትራውያን የወገናችሁን ሂወት ለማትረፍ ሌት ተቀን እየሰራችሁት ላለው ሰብአዊ ተግባር በራሴ፣ በትግራይ መንግስትና ህዝብ ስም ላመሰግን እወዳለሁ ያሉት ፕሬዝዳንት ታደሰ እንደ ሕፃፅ ሁሉ ተፈናቃዮች ባሉባቸው ሌሎች 145 መጠለያ ጣብያዎችም በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

የጀመራችሁት ሰብአዊና የተቀደሰ ተግባር ተዳክሞ የቆየውን የጋራ እሴት በማጎልበት ረገድ የራሱን አስተዋፅኦ ያበረክታልና አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉበት ጥርዬን አስተላልፋለሁ በማለትም ለህዝቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢፌዴሪ መንግስት፣ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስታትና መላው የኢትዮዽያ ህዝቦች፣ በትግራይ ጦርነት ምክንያት ከየቄያቸው ተፈናቅለው በሞት ኣደጋ ላይ ያሉትን ወገኖች ህይወት መታደግና ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ማድረግ ከውዴታም በላይ ግዴታ ነውና የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ ከኣክብሮት ጋር ጥሪዬን ኣቀርባለሁ ሲሉም መልእክት ልከዋል፡፡

እንደሚታወቀው ለዚህ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ማኖር የሚቻለው እነዚህን ተፈናቃዮች ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ቄያቸው መመለስና ማቋቋም ሲቻል ነው ያሉት ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ የፌደራል መንግስት አሁንም ለዚህ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ተፈናቃዮችን ወደ ቦታቸው በተቻለ ፍጥነት እንዲመለሱ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሰሙኑን ብትግራይ ከሚገኙ 146 የተፈናቃዮች ካምፖች አንዱ በሆነው ሕፃፅ 1700 ሰዎች በረሃብ ምክንያት በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ የወጡ ምስሎች ተከትሎ ትልቅ አጀንዳ የሆነ ሁኖ በማእከሉ እስካሁን 350 ተፈናቃዮች በረሃብ መሞታቸው ታውቀዋል፡፡

እንዲሁም ዓዲ መሐመዳይ በሚባል ሌላ ማቆያ ማእከል 283 ተፈናቃዮች በረሃብ ሲሞቱ 6630 ሰዎች በከፍተኛ ረሃብ እንደሚገኙ መረጃዎች አሳይተዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates