ዲፕሎማሲ
የኬኒያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 14/04/2018፡- ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶን መቀበላቸው መረጃው አመልክቷል።
“ዛሬ የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ተቀብያለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው” ብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት ፅሑፍ “በውይይታችን የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ የተለዋወጥን ሲሆን ይኽም በሰላም እና መረጋጋት፣ ንግግር ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነበር” ሲሉ አክሏል።



