ኢኮኖሚ

በትግራይ ክልል ህጻፅ መጠለያ ጣቢያ በሚገኙ በርካታ ተፈናቃዮች እየተባባሰ በመጣ የረሃብ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 14/04/2018፡- በከፋ የምግብ እጥረትና በውስን የህክምና አገልግሎት ምክንያት ተደጋጋሚ ሞት እየተመዘገበ መሆኑንና በርካታ ሰዎች በአስከፊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ዘገባዎች አመላክተዋል።

በዚህ ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኃላ 350 ሰዎች በረሃብ ሲሞቱ 1700 ደግሞ በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች አሳይቷል።

አረጋውያን፣ ሴቶችና ህጻናት ዋነኛ ተጎጂዎች ሲሆኑ፣ ነዋሪዎች ለቀናት የሚበሉት በማጣታቸው ምክንያት ተዳክመው እንደሚወድቁ ተገልጿል።

የሚቀርብላቸው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነና አልፎ አልፎ የሚሰጣቸው 15 ኪሎ ግራም እህል መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እንደማያሟላም ገልጸዋል።

በጦርነት ወቅት ከምዕራብ ትግራይ የተፈናቀሉት እነዚህ ዜጎች እህሉን ለማስፈጨትና ለሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መሠረታዊ ነገሮች ወጪም ለመሸፈን ግማሹን እህል ለመሸጥ እንደሚገደዱ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የሚቀርበው የእህል ዓይነት ለህጻናት፣ ለአረጋውያንና ለታመሙ ሰዎች ለመመገብ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቁመዋል።

ችግሩ የህፃፅ ተፈናቃዮች መጠሊያ ጎልቶ ቢታይም በሁሉም የተፈናቃይ ካምፖች ተመሳሳይ ችግሮች እንዳሉ እየተነገረ ነው።

በተመሳሳይ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ 282 ተፈናቃዮች በአዲ መሐመዳይ የስደተኞች ካምፕ በረሃብ መሞታቸው ተገልጿል።

ባለፉት ሰባት ወራት ውስጥ ከ6,630 በላይ ተፈናቃዮች በሰብአዊ እርዳታ እጥረት ምክንያት ለከባድ ረሃብ እንደተጋለጡም መረጃዎች ጠቁሟል።

የአዲ መሐመዳይ ማዕከል ከ27,300 በላይ ተፈናቃዮች የሚገኙበት ሲሆን አብዛኛዎቹ ህፃናት፣ እናቶች እና ተጋላጭ አረጋዊያን ናቸው።

የፕሪቶሪያው ስምምነት ከያዛቸው ነጥቦች ተፈናቃዮች ደህንነታቸው ተጠብቆ በአስቸኳይ መመለስ የሚል አንዱ ቢሆንም ለሶስት ዓመታት ሳይመለሱ አሁንም በረሃብ እየሞቱ ይገኛሉ።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates