ዲፕሎማሲ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሃያ በላይ አምባሳደሮቻቸው ከተለያዩ አገራት መጥራታቸው ተሰማ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 14/04/2018፡- ትራምፕ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ጨምሮ በ15 የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙን ጨምሮ ከሃያ በላይ አምባሳደሮቻቸውን ወደ ዋሽንግተን መጥራታቸው ተገልጿል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያን፣ ሶማሊያን እና ጅቡቲን ጨምሮ በ15 የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ አምባሳደሮቻቸውን ወደ ሀገራቸው ጠርተዋል።

እርምጃው ያልተለመደ ነው የተባለ ሲሆን፣ ዩናይትድ ስቴትስ በውጭ ሀገራት ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ውክልና መልሳ ለማዋቀር የምታደርገው ሰፊ ጥረት አካል ነው ተብሏል።

በዲፕሎማሲያዊ ማኅበረሰብ ምንጮች እየተዘዋወረ ባለው መረጃ መሠረት፣ አሜሪካ አምባሳደሮቿን ወደ ሀገሯ የጠራችባቸው የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝር የተለያዩ የአህጉሪቱን ቀጠናዎች ያካተተ ነው።

ዝርዝሩ በሰሜን አፍሪካ የሚገኙትን ግብፅ እና አልጄሪያን ጨምሮ በአፍሪካ_ቀንድ፣ በምስራቅ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛውና በደቡባዊ_አፍሪካ የሚገኙ ሀገራትን ያጠቃልላል።

አምባሳደሮቹ እንዲመለሱ ስለተደረገበት ምክንያት እስካሁን የተሰጠ ይፋዊ ማብራሪያ የለም የተባለ ሲሆን፤ ክፍት የሆኑትን የሥራ መደቦች ለመተካት ግልጽ የሆነ የጊዜ ሰሌዳ አለመቀመጡም ተመላክቷል።

ውሳኔው በአፍሪካ ቀንድ በሶማሊያ፣ በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ የሚገኙ የአሜሪካ አምባሳደሮችን እንደሚመለከት የተነገረ ሲሆን ቀጠናው በዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች መተላለፊያነቱ፣ በአሜሪካ የጦር ሰፈር መገኘት እና በፀረ-ሽብር ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ ለዋሽንግተን ስልታዊ ፋይዳ ያለው አካባቢ መሆኑ ተጠቁሟል።

በሰሜን አፍሪካ ደግሞ ግብፅ እና አልጄሪያ በዝርዝሩ ውስጥ ከተካተቱት ሀገራት መካከል ይገኙበታል። ሁለቱም ሀገራት በጸጥታ እና በኢነርጂ ጉዳዮች ላይ ለአሜሪካ ቁልፍ ቀጠናዊ አጋሮች እንደሆኑ ይታሰባል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates