አፍሪካ

ኬንያውያን ሰልፈኞች በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ያለውን ግጭትና ጦርነት ቀውስ በተመለከተ የዓለም አቀፉን ማሕበረሰብ ዝምታ ነቀፉ።

ኢትዮ ሞኒተር፡13/04/2018፡- ከነዋሪዎች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ከሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች የተውጣጡ ኬንያውያን ሰልፈኞች በሞምባሳ ከተማ ለሳምንታት የዘለቀ የሰላም ጉዞና ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።

ሰልፈኞቹ ሱዳንና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እየተካሄደ ያለው ግጭትና የእርስ በእርስ ጦርነት፣ በንጹሐን ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳትና ሰብዓዊ ቀውስ እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ብዙም ለጉዳዩ ትኩረት አልሰጠውም በሚል ተችተዋል።

በተለይ በሱዳን ላለፉት ሶስት ዓመታት እየተካሄደ ያለው ጦርነት የውጭ ሐይሎች ጣልቃ ገብነት ያለው እና የዓለም ማህበረሰብ የነፈገው ነው በማለት ብዙዎች ይወቅሳሉ።

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ አሜሪካን ጨምሮ ግብፅ፣ ኢሚሬትስ እና ሳውዲ ዓረብ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ቢንቀሳቀሱም ያን ያህል ውጤት እያስገኘ ነው ተብሎ አይታሰብም።

ለጦርነቱ በተለያየ መንገድ ድጋፍ የሚያደርጉ አገራት ሸምጋይ ሆኖ መቅረባቸው ደግሞ ውጤት እንዳያመጣ ካደረጉት ጉዳዮች አንድ ነው ተብሎ ይታመናል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates