ዲፕሎማሲ

በኤርትራ የታገቱትን 3 የአዘርባጃን መርከቦች ለማስለቀቅ ጥረት መጀመሩ ተገለፀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡13/04/2018፡- ከአንድ አመት በፊት 3 የአዘርባጃን መርከቦች በስዊዝ ካናል በኩል አድርገው ወደ ተባበሩት አረብ ኢመሬትስ እየተጓዙ ሳለ ድንገት የኤርትራን የውሀ ክልል ጥሰው መግባታቸው ተገልፆ ነበር፡፡

በዚህ የኤርትራ ባህር ሀይል አባላት እነዚህን መርከቦች በቁጥጥር ስር ያዋሉዋቸው ሲሆን ከመርከቦቹ ጋር 18 የመርከብ ሰራተኞችና ስድስት የታጠቁ የደህንነት ሰራተኞችም በቁጥጥር ስር ውለው ነበር፡፡

18ቱ መርከበኞች የአዘርባጃን ዜጎች ሲሆኑ ለበርካታ ወራት ያህል ከታሰሩ በኋላ መለቀቃቸውን ይታወቃል፡፡
እንዲሁም ስድስቱ የሲሪላንካ ዜግነት ያላቸው የደህንነት ሰራተኞች ደግሞ ለአንድ አመት ያህል በተደረገ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ከወራት በፊት ከእስር ተለቀው ወደ አገራቸው ሄደዋል፡፡

ሆኖም 3ቱ መርከቦች አሁንም በኤርትራ ቁጥጥር ስር በአሰብ ወደብ ቆመው እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የቫንጋርድ ቴክኖሎጂ የኢንተለጀንስ ሀላፊ ኤሊ ሻፊክ እንደሚናገሩት መርከቦቹ ንብረትነታቸው የአዘርባጃን የግል ተቋም ሲሆን በቁጥጥር ስር ከዋሉ ጀምሮ ከኤርትራ መንግስት ጋር ግንኙነት እየተደረገ ነው፡፡

ታስረው የነበሩት መርከበኞች እንዲለቀቁም የማስተባበር ስራ ማከናወናቸውን አስረድተዋል፡፡

“የመርከቦቹ ካፒቴኖች የገለፁት ከባድ ንፋስ ስላጋጠማቸው ፈቃድ ሳይጠይቁ ወደኤርትራ ባህር ክልል ውስጥ መግባታቸውን ነው›› ያሉት ሀላፊው በዚህ ላይ ምርመራው በመጠናቀቁ መርከበኞቹና የደህንነት ሰራተኞቹ መለቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡

እነዚህ 3 መርከቦች የጫኑትን እቃ በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያዎች በርካታ ግምታዊ አስተያየቶች ሲሰጡ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን የቫንጋርድ ቴክሎኖጂ የኢንተለጀንስ ሀላፊው መርከቦቹ ምን ጭነው እንደነበር ተጠይቀው መልስ ሰጥተዋል።

3ቱም መርከቦች “ታግ ቦት” የሚባሉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ታግ ቦቶች ሀይለኛ ሞተር ያላቸውና ትልልቅ መርከቦችን ወደ ወደብ የሚጎትቱ፣ እንዲሁም በባህር ላይ የተበላሹ መርከቦችን የሚያነሱ መሆናቸውን አስረድቷል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates