አፍሪካ
የሱዳን ሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት ሊቀመንበር እና የጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ ሌተናንት ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ዛሬ በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ለአንድ ቀን ይፋዊ ጉብኝት ደርሰዋል።
በግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ በካይሮ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አቀባበል ተደርጎላቸዋ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/04/2018፡- ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን በማሻሻል እና በማዳበር በተለያዩ ዘርፎች የጋራ ትብብርን ለማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የጋራ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ጄነራል አልቡርሃን ባለፉት ሁለት ቀናት ሳውዲ ዓረብ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡
በሪያድ ቆይታቸውም ከሳውዲ ልኡል ቢን ሳልማን በተለያዩ ጉዳዮች መወያየታቸው ተዘግበዋል፡፡
እንዲሁም ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ልዩ አማካሪ ማሳድ ቦሎስ መወያየታቸው ይታወሳል፡፡


