ፖለቲካ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ከፌዴራል መንግስት ጋር ለመወያየት አዲስ አበባ እንደሚገኙ ተገለፀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/04/2018፡- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ትላንት ከመቐለ ተነስተው አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ከፌዴራል መንግስት ጋር ለሚደረገው ውይይት ልዑካን ቡድኑን እየመሩ አዲስ አበባ ማቅናታቸውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ቢሮ ባወጣው አጭር መግለጫ አስታውቋል።

ቢሮው ትናንት ከሰዓት በኋላ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ያወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው፤ የጉብኝቱ ዓላማ ከፌዴራል ባለስልጣናት ጋር በ “አጠቃላይ ጉዳዮች” ላይ ለመወያየት ነው።

ይሁን እንጂ መግለጫው ስለ ውይይቱ ዝርዝር አጀንዳም ሆነ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ የሚያገኟቸውን የፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ማንነት አልጠቀሰም።

ከፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ ጋር ምክትላቸው አቶ አማኑኤል አሰፋ እና የውሃ ቢሮ ሓላፊው አቶ ተክላይ ገ/መድህን ተጉዘዋል፡፡

ውይይቱ ክልሉ ተቋረጠብኝ ባለው በጀት፣ ነዳጅ እንዲሆም አጠቃላይ የፕሪቶሪያ አፈፃፀም ሊሆን እንደሚችል እየተዘገበ ይገኛል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates