ኢትዮጵያ

የጋምቤላ ክልል የትኛውንም የጦር መሳሪያ ይዞ የሚገኝ እና የሚንቀሳቀስ ግለሰብ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድበት አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/04/2018፡- የጋምቤላ ክልል መንግስት ለፀጥታ ስራ ተመድበው ከሚሰሩ የሰራዊት አባላት ውጪ የትኛውንም የጦር መሳሪያ ይዞ የሚገኝ እና የሚንቀሳቀስ ግለሰብ ወይም ቡድን ላይ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስዱ መሆኑን አስገንዝቧል።

ባለፉት ተከታታይ ቀናት በጋምቤላ ክልል በተፈጸሙ ጥቃቶች የጋምቤላ ከተማ የፖሊስ አዛዥን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች መገደላቸው የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ካለፉት ሳምንታት ወዲህ በዋና ከተማዋ ጋምቤላ እና በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ውስጥ በሚፈጸሙ ጥቃቶች የተነሳ አለመረጋጋት መፈጠሩን የተገለፀ ሲሆን

ማንነታቸውን በውል ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈጸሟቸው ጥቃቶች የፀጥታ አባላት እና ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እንዲሁም የነዋሪዎች የዕለት ከዕለት መደበኛ እንቅስቃሴ መስተጓጎሉ ተዘግበዋ።

የክልሉ ዋና ከተማ የፖሊስ አዛዥ በተፈጸመባቸው ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡሞድ እና ምክትላቸው ዶ/ር ጋትሉዋክ ሮን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ይህንንም ተከትሎ በጋምቤላ ክልል፣ ረቡዕ ታኅሣሥ 8 ቀን 2018 ዓ. ም. ከረፋድ ጀምሮ ተኩስ ይሰማ እንደነበር ነዋሪዎች ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን፣ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን መስማታቸውን ገልጸዋል።

የጋምቤላ ክልል አስተዳደር ረቡዕ ምሽት ባወጣው መግለጫ “የክልሉ ሕዝብ ሰላም እንቅልፍ የሚነሳቸው እና ግጭት እና የሰው ሞት የሚያስደስታቸው” ያላቸው በስም ያልጠቀሳቸው ኃይሎች ከሰሞኑ የጋምቤላ ከተማን ጨምሮ በሌሎች ወረዳዎች ትርምስ ፈጥረዋል በማለት የተከሰተውን ሁኔታ ገልጾታል።

ጨምሮም እነዚህ ኃይሎች “ሰዎችን በመግደል፣ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት በማድረስ እና ሕይወት እንዲጠፋ በማድረግ፣ የፀጥታ አካላትን እና አመራርን ዒላማ በማድረግ” የተለያዩ ሙከራዎችን ማድረጋቸውን ገልጿል።

ክልሉ ከፌደራል የጸጥታ አካላት በመሆን ድርጊቱ የፈፀሙት አካላት በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየሰራ እንደሆነ የገለፀ ሲሆን ለፀጥታ ስራ ተመድበው ከሚሰሩ የሰራዊት አባላት ውጪ የትኛውንም የጦር መሳሪያ ይዞ የሚገኝ እና የሚንቀሳቀስ ግለሰብ ወይም ቡድን ላይ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስዱ መሆኑን አስገንዝቧል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates