ዲፕሎማሲ

ኢትዮጵያና ሕንድ ያላቸው ሁለንተናዊ ትብብር ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠ/ሚ ናሬንድራ ሞዲ ተናገሩ፡፡

ለሁት ቀናት አዲስ ኣበባ የገቡት የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በፓርላማ ተገኝቶ ንግግር አድርገዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 08/04/2018፡- ኢትዮጵያና ሕንድ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸው ሁለንተናዊ ትብብር ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢፌዴሪ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በአፍሪካ ቅኝ ግዛትን በመገርሰስ ሒደት የአንበሳውን ድርሻ በተወጣችው ኢትዮጵያ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ተገኝቼ መልዕክት በማስተላለፌ ክብር ተሰምቶኛል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ እና ሕንድ ዲፕሎማሲያዊና ዘርፈ ብዙ ግንኙነት በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑን በመግለፅ ኢትዮጵያ እና ሕንድ የሕዝብ ለሕዝብ፣ የታሪክ እንዲሁም የባሕል ትስስር ያላቸው ሀገራት እንደሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያና ሕንድ ሁለንተናዊ ትብብር ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።

በተለይም በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሳይበር ደህንነት፣ አቅም ግንባታ፣ ግብርና፣ ትምህርት እና ጤና ዘርፎች ላይ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ጠ/ሚ ናሬንድራ ሞዲ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ከተለያዩ ባለስልጣናት ውይይቶች ማድረጋቸው ተገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል የክብር እራት ግብዣ ባደረጉላቸው ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተሻገረ ክስተት መሆኑን ገልጸዋል።

ጉብኝቱ ጥንቃቄ የተሞላበት ዕቅድ እና በደፋር ሀሳቦች ለውጥን ማራመድ እንደሚችሉ የተረዱ የሁለት ሀገራት መሰባሰብ እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህም ረጅም እና ጥልቅ የሆነው የኢትዮጵያ እና ህንድ የትስስር ታሪክ ወሳኝ የሆነው የትብብር ጉዞ ምዕራፍ ወደፊት የሚቀጥል መሆኑን ማሳያ እንደሆነ አስረድተዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates