እስራኤል በያዘችው ምስራቅ ኢየሩሳሌም ውስጥ 9,000 ቤቶች ለመገንባት ማቀድዋ ተገለፀ፡፡
ይህም ወደፊት የፍልስጤም መንግሥት እንዳይኖር ለማረጋገጥ ነው ተብለዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 08/04/2018፡- የእስራኤል ባለስልጣናት በተያዘችው ምስራቅ ኢየሩሳሌም ውስጥ በቃላኒያ አየር ማረፊያ ቦታ ላይ 9,000 አዳዲስ የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ዕቅዶች እንደያዙ የዘገበው አልጄዚራ፣ ይህም የፍልስጤም መሬቶችን እርስ በእርስ እንዳይገናኙ ለማድረግ እና በአከባቢው የፍልስጤም መንግሥት እንዳይፈጠር ለማድረግ ሌላ ሙከራ ነው ተብለዋል።
በሰሜን ምስራቅ ኢየሩሳሌም የሚገኘው የአታሮት ሰፈር ተብሎ የሚጠራው፣ የፍልስጤም መንግሥትን ለማዳከም የE1 ዕቅድን የሚያስታውስ፣ ዛሬ በዲስትሪክት ፕላን እና ህንፃ ኮሚቴ ዝርዝር ስራዎቹ እንደሚፀድቅ የእስራኤል ፒስ ናው ቡድን ገልጿል።
አዲሱ ሰፈራ በሕዝብ በተጨናነቀው የፍልስጤም ከተማ ውስጥ እንደሚገነባ የታቀደ ሲሆን፣ ይህም ከተያዘው ዌስት ባንክ ከራማላህ እና በሰሜን በኩል ቃላኒያ የስደተኞች ካምፕ፣ እስከ አር-ራም፣ ቤት ሃኒና እና ቢር ናባላ ድረስ ይዘልቃል ተብለዋል።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን በአቅራቢያው በሚኖሩበት አካባቢ የእስራኤልን ግዛት ይገነባል፣ ይህም በአንድ ቁልፍ ቦታ ላይ ልማትን ለማገድ እና ሉዓላዊ የፍልስጤም መንግሥት የመመስረት እድልን የበለጠ ለማበላሸት ነው ብለዋል ዘገባው።
“ይህ አውዳሚ እቅድ ከተተገበረ ምስራቅ ኢየሩሳሌምን ከአካባቢው የፍልስጤም አካባቢ ጋር የማገናኘት እድልን የሚከላከል እና በተግባር ከእስራኤል ጎን ለጎን የፍልስጤም መንግሥት እንዳይመሠረት የሚያግድ ነው” ሲል ፒስ ናው ቡድን አስጠንቅቀዋል።
እስራኤል እ.አ.አ. ጥቅምት 2023 ከጀመረው በርካታ ዋና ዋና ፕሮጀክቶችን በማካሄድ ሕገ-ወጥ ሰፈሮችን ለመገንባት እና የተቆጣጠረችውን ዌስት ባንክን ለመውረስ እየሞከረች ነው በማለት እየተከሰሰች ትገኛለች፡፡
ባለፈው ሳምንት የእስራኤል የደህንነት ካቢኔ በዌስት ባንክ 19 ሕገ-ወጥ ሰፈሮችን ለማቋቋም ባወጣው ዕቅድ ላይ ተፈራርሟል።



