ኢትዮጵያ

ከ5000 በላይ የኢትዮጵያ ዜጎች በአዲሱ የአሜሪካ ውሳኔ ተጠቂ ይሆናሉ ተባለ።

አሜሪካ ከሰሞኑ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ትሰጥ የነበረውን ጊዜያዊ የህግ ከለላ ማቋረጧ ይታወሳል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 07/04/2018፡- 5001 ኢትዮጵያውያን የህግ ከለላ ተሰጥቷቸው እንደነበርና 263 የሚሆኑ ተጨማሪ ዜጎች አመልክተው በመጠባበቅ ላይ እንደነበሩ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

አሜሪካ በፈረንጆቹ ታህሳስ 12 ቀን 2022 በኢትዮጵያ የነበረውን ግጭት ተከትሎ ለኢትዮጵያ ዜጎች ጊዜያዊ የህግ ከለላ መስጠት የጀመረች ሲሆን በሚያዚያ 2024 ዳግም አራዝማው ነበር።

አሜሪካ በ2022 በትግራይ እና ኦሮሚያ ክልሎች የነበሩ ግጭቶች ይህ የጊዜያዊ ከለላ እንዲሰጥ ምክንያት ነበሩ ስትል የትግራዩ ጦርነት በሰላም ስምምነት መቋጨቱንና በኦሮሚያም ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አካል ጋር ክልሉ የሰላም ስምምነት መፈራረሙን፣ ታጣቂዎች መግባታቸውንና ከስምምነቱ በኋላ ግጭት መቀነሱንም አንስታለች።

አሜሪካ የትግራዩ ጦርነት ሲገባደድ በአማራ ክልል ግጭት መቀስቀሱን ጠቅሳ በመንግስት እና ፋኖ መካከል ያለው ግጭት መቀነሱን ንፁሃን ግን ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩ አንስታለች።

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የተመላሽ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት ስጋት ውስጥ የሚከት ነገር እንደሌለ እና የሀገር ውስጥ መፈናቀሎች ቀንሰዋል ያለችው አሜሪካ የምግብ እና ማህበራዊ አገልግሎቶች መሻሻላቸውን ለዚህም ማሳያው አሜሪካ ራሷ በሰሜን ኢትዮጵያ ትሰጥ የነበረውን የምግብ ድጋፍ ፕሮግራም ለጣምራ ኮሚቴ ማስተላለፏን አንስታለች።

ከ2022-2025 ድረስ 2147 የኢትዮጵያ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የጉዞ ሰነድ መጠየቃቸውንም በጥሩ ጎን ተመልክቼዋለሁ ብላለች።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates